በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የንግድ ተቋማት እስከ ም...

image description
- In ንግደረ    0

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የንግድ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3:30 ድረስ እንዲሰሩ የወጣው ደንብ ቁጥር 185/2017 አስመልክቶ ከፍተኛ መሻሻል እየታየ መሆኑ በተደረገው ምልከታ መረጋገጡ ተገለፀ::

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የንግድ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3:30 ድረስ እንዲሰሩ የወጣው ደንብ ቁጥር 185/2017 አስመልክቶ ከፍተኛ መሻሻል እየታየ መሆኑ በተደረገው ምልከታ መረጋገጡ ተገለፀ::

****************

ሚያዝያ 2-2017ዓ.ም

በምሽት የንግድ እና ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ የወጣውን ደንብ ቁጥር 185/2017 አስመልክቶ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አይዳ አወል እንዲሁም የገበያ ማረጋጋት ግብረ ሀይል አባላት በጋራ በመሆን በክፍለ ከተማው ውስጥ ተዘዋውረው ምልከታና ቅኝት አድርገዋል::

በምሽት የንግድና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ የተፈለገው የከተማዋን ፈጣን እድገት ተከትሎ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ለማሳደግ እንደሆነ የገለፁት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን በተደረገው ምልከታ መረጋገጡን ገልፀዋል::

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አይዳ አወል በበኩላቸው በክፍለ ከተማችን የሚገኙ የንግድ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አዋጁን በተገቢው መንገድ ተግባራዊ በማድረግ እየተነቃቃ የመጣው ኢክኖሚያዊ እድገት ላይ የበኩላቸውን አሻራ ማሳረፍ ይኖርባቸዋል ብለዋል::

የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ይድነቃቸው ግርማ በበኩላቸው መዲናችን አዲስ አበባ የበርካታ ዲፕሎማቶች መቀመጫ በመሆኗ ከዓለም አቀፍ ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ እንድትሆን እና እንድትነቃቃ አዋጁን ተግባራዊ ማድረግ የሁሉምች ህብረተሰብ ክፍል ትብብር የሚጠይቅ በመሆኑ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል::

የንግድ ተቋማቱ እስከ ምሽቱ 3፡30 ድረስ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎቹ ደግሞ እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ አገልግሎት መስጠት የሚኖርባቸው መሆኑ የወጣው አዋጅ ላይ መረዳት ይቻላል::


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments