
ከ15 እስከ 25 በመቶ የዋጋ ቅናሽ የተደረገበት ባዛር መከፈቱን የአራዳ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት አስታወቀ።
ከ15 እስከ 25 በመቶ የዋጋ ቅናሽ የተደረገበት ባዛር መከፈቱን የአራዳ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት አስታወቀ።
ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም
የአራዳ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ከሚያዝያ 3 እስከ ሚያዝያ 11/2017 ዓ.ም የሚቆይ የፋሲካ በአል ባዛር የከተማ፣ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ ነጋዴዎችና ሸማቾች በተገኙበት ፒያሳ ጊዮርጊስ አደባባይ በይፋ አስጀመረ።
ባዛሩን በንግግር ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የፋሲካ በአልን ምክንያት በማድረግ ምንም አይነት የምርት እጥረትና የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመጣመር በእቅድ ተይዞ እየተገመገመ ሲሰራ እንደነበር ገልጸው በከተማው ውስጥ ከሚዘጋጁት 14 ባዛሮችና 210 የሰንበት ገበያዎች የዛሬው የመጀመሪያው ነው ብለዋል።
ምንም አይነት የዋጋ ንረትም ሆነ የምርት እጥረት እንደማይፈጠር የገለጹት ወ/ሮ ሀቢባ ከፍተኛ ቅናሽ የተደረገባቸውን የተለያዩ ምርቶች ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ በነቂስ ወጥቶ እንዲጎበኝና አቅሙ የፈቀደውን እንዲሸምት ጋብዘዋል።
የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች የከተማ አስተዳደሩ በከተማው ውስጥ የዋጋ ንረትና የምርት እጥረት እንዳይከሰት የሚሰራቸውን ስራዎች በከፍተኛ ደረጃ የሚያጠናክሩ ናቸው ያሉት የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌታሁን አበራ በዛሬው እለት የተከፈተው ባዛር ሰፊና ማዕከላዊ ቦታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ የክ/ከተማው ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም የከተማው ነዋሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ሊጠቀሙበት የሚያስችል ነው ብለዋል።
የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላይነህ ሙሉጌታ በበኩላቸው በዛሬው እለት የተከፈተውን ባዛር ጨምሮ በ17 የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲሁም የእንስሳት ተዋጽኦ ከመደበኛው ገበያ ከ15 እስከ 25 በመቶ ቅናሽ ተደርጎባቸው መቅረባቸውንና ባዛሩ ለ9 ቀናት የሚቆይ መሆኑን በመግለጽ ሸማቹ ማህበረሰብ የቀረበለትን እድል በአግባቡ እንዲጠቀም ጋብዘዋል።
ባዛሩ የዋጋ ንረትና የምርት እጥረት እንዳይፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለው እንደሚጠብቁና አሁን የቀረበው ምርት ከፍተኛ ጥራትና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው መሆኑን አስተያየታቸውን የሰጡ ሸማቾች ተናግረዋል።
ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069351701097
https://t.me/Addisababatradebureau
https://vm.tiktok.com/ZMB4AxNvr/
https://youtube.com/@addisababatradebureau-s2d...
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments