በመዲናችን መጪዉን የፋሲካ በዓል አስመልክቶ የተ...

image description
- In ንግደረ    0

በመዲናችን መጪዉን የፋሲካ በዓል አስመልክቶ የተረጋጋና ፍትሃዊ የሆነ የግብይት ስርዓት እንዲኖር በልዩ ትኩርት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

በመዲናችን መጪዉን የፋሲካ በዓል አስመልክቶ የተረጋጋና ፍትሃዊ የሆነ የግብይት ስርዓት እንዲኖር በልዩ ትኩርት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

*********************

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሚያዚያ 06/2017

ይህ የተገለፀዉ የገበያ መረጋጋት፤የገቢ መሰብሰብ፤ ህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር እና የኢትዮጵያ-አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ግብረ-ሀይል በመዲናችን መጪዉን የፋሲካ በዓል አስመልክቶ የተረጋጋና ፍትሃዊ የሆነ የግብይት ስርዓት እንዲኖር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በገመገመበት ወቅት ነዉ፡፤

ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ እንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የግብረ ኃይሉ ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደተናገሩት ለመጪው የትንሳኤ በዓል ለገበያ የቀረቡ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች፤የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች፤የኢንዱስትሪ ምርት ዉጤቶች ፤የግብርና ዉጤቶች እና የቁም እንሰሳት አቅርቦት በበቂ መኖሩን ገልፀዋል፡፡

እነዚህ ምርቶች በተገቢው ሁኔታ እንዲሰራጩ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ከማእከል እስከ ወረዳ አስፈላጊው ድጋፍና ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዉ አሁንም የምርት አቅርቦቱን፤የግብይት ዋጋዉን እንዲሁም የመሸጫ ቦታዎችን የማስፋት ስራዎችን ጨምሮ በተደራጀ የስምሪት አግባብ በወጥነት የመስክ ምልከታ በማድረግ የድጋፍና የቁጥጥር ስራዎችን ይበልጥ ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩልም በእንቁላል ላይ የሚታየዉን ያልተረጋጋ የዋጋ እና የስርጭት መዋዠቅ ግብረ-ሃይሉ ክፍተቱን ፈጥኖ በመገምገም ችግሩን መፍታትና ከአቅራቢዎች ጋር የተጀመረዉን የትስስር ስራ ይበልጥ በማሳለጥ እቅርቦቱን ማሳደግ እንደሚገባም ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ጨምሮ በዘላቂነት በምርት አቅርቦት፤በህግ ማስከበር፤በኢመደበኛ ንግድ፤በምሽት ንግድ እንቅስቃሴ፤በገቢ አሰባሰብ እና በሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ላይ የተሰሩ ስራዎችንና የመጡ ለዉጦችን በማስቀጠል በቀጣይም አሰራራችንን በማስፋት በመዲናችን የተረጋጋና ፍትሃዊ የሆነ የግብይት ስርዓት እንዲኖር ሁሉም በባለቤትነት የድርሻዉን በልዩ ትኩረት እንዲወጣ ሲሉ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት

https://www.facebook.com/profile.php?id=100069351701097

https://t.me/Addisababatradebureau

https://vm.tiktok.com/ZMB4AxNvr/

https://youtube.com/@addisababatradebureau-s2d...


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments