
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከላፍቶ አትክልት ተራ ነጋዴ የማህበረሰብ ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከላፍቶ አትክልት ተራ ነጋዴ የማህበረሰብ ጋር ውይይት ተካሂዷል።
ሚያዚያ 23/2017
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ ፣የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ጨምሮ ሌሎች የንግድ ቢሮ እና የክፍለ ከተማው የዘርፍ አመራሮች እንዲሁም የላፍቶ አትክልት ተራ ነጋዴዎች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው የአተክልት ተራ ግቢው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መስሪያ ቦታና ለሸማች የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት መስጪያ በመሆኑ በአግባቡና በስርዓት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ህግና ስርዓትን በመከተልና ከመንግስት የፀጥታ አካል ጋር በመሆን ህገ ወጥ ተግባራትን ሲከላከሉ የነበሩ ነጋዴዎችን አመስግነው ነጋዴዎች ስራውን በትኩረት መስራት እንዳለባቸው በመጥቀስ ቀጣይ የስራ ቦታውን ማዘመንና ምቹ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ የንግድ ግብረ ኃይል ህገ ወጥ ተግባራትን፣ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በማስተካከል ረገድ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments