
ቢሮው ከሐረሪ ክልል ከመጡ ተወካዮች ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄደ፤
ቢሮው ከሐረሪ ክልል ከመጡ ተወካዮች ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄደ፤
========================
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ ሐምሌ 2/2017 ዓ.ም.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከሐረሪ ክልል ንግድ ልማትና እንዱስትሪ ኤጀንሲ ተወካዮች ጋር ተቋማዊ የመዋቅር አደረጃጀትና አሰራርን በሚመለከት ልምድ ልውውጥ አካሂዷል።
የልምድ ልውውጥና የውይይት መድረኩን ያስጀመሩትና የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ስለ ቢሮው አጠቃላይ አሰራር አጭር ማብራርያ ከሰጡ በኋላ፣ የቢሮዉ ዳይሬክቶሬቶች በየዘርፋቻው ስለአደረጃጀታቸውና አሰራራቸው ርፖርቶችን አቅርበዋል።
በመጨረሻም የሐሪር ክልል ንግድ ልማትና እንዱስትሪ ኤጀንሲ ኃላፊ አ/ቶ ሸረፋ ሙሜ የቢሮዉ አሰራርና አካሄድ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው የክልሉን ንግድ ልማትና እንዱስትሪ ኤጀንሲ አሰራርን በተመለከተ ልምድ አካፍለዋል።
ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069351701097
https://t.me/Addisababatradebureau
https://vm.tiktok.com/ZMB4AxNvr/
https://youtube.com/@addisababatradebureau-s2d...
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments