2ኛው ከተማ ዓቀፍ "የኢትዮጵያን ይግዙ" የንግድ...

image description
- In ንግደረ    0

2ኛው ከተማ ዓቀፍ "የኢትዮጵያን ይግዙ" የንግድ ሣምንት "የኢትዮጵያ ምርት ለብልፅግና "በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽንማዕከል ባዛር ተከፈተ።

2ኛው ከተማ ዓቀፍ "የኢትዮጵያን ይግዙ" የንግድ ሣምንት "የኢትዮጵያ ምርት ለብልፅግና "በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽንማዕከል ባዛር ተከፈተ።

====================

"አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሐምሌ 11/2017

የአዲስ አበባ ከተማ ምትክል ከንትባ እና እንዱስትሪ ቢሮ ኃላፍ አቶ ጃንጥራር እንደተናገሩት ምርቶችን ከአምራቾች በቀጥታ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ለማድረስ በተሠሩ ሥራዎች ይስተዋሉ የነበሩ መስተጓጎሎችን ማስቀረት ተችሏል፡፡በዚህም የንግዱ እንቅስቃሴ በሕጋዊ በመንገድ ብቻ እንዲከናወን ተደርጓል ብለዋል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አብደላ ሀኪም ሙሉ በበኩላቸው፤ የንግዱ ዘርፍ ስብራቶችን፣ ብልሹ አሠራሮች እና ሕገ ወጥነትን ለመከላከል እየተሠራ ነው መሆኑን ገልጸዋል።

በሀገር ደረጃ የኢትዮጵያ ምርት ለማስተዋወቅ፣ የሀገሪቱን የንግድ ሥርዓት ለማዘመን፣ ምርቶችን ህብረተሰቡ እንዲጠቀም ለማድረግ እየተሠራ ነው ሲሉ አክለዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጂ "የኢትዮጵያን ይግዙ" የንግድ ሣምንት የከተማውን ህብረተሰብ የኑሮ ጫና ለማቃለል የሚደረግ ተግባር አካል መሆኑን ጠቅሰዋል።

በከተማው ገበያ ማዕከላትን ማሳደግ፣ የቅዳሜ እና ዕሁድ ገበያ ማስፋፋት፣ የንግዱን ሥርዓት ሕጋዊ ማድረግ እና ሌሎች የኑሮ ጫናዎችን ለማቃለል የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት

https://www.facebook.com/profile.php?id=100069351701097

https://t.me/Addisababatradebureau

https://vm.tiktok.com/ZMB4AxNvr/

https://youtube.com/@addisababatradebureau-s2d...


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments