የ2017 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ “በተሳለጠ ንግድ ወደሚጨበጥ ሀገራዊ ተስፋ” በሚል መሪ ቃል የዓመቱ ስኬታችን ትሩፋት በሆነው የጥራት መንደር እየተካሄ ነው፡፡
የ2017 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ “በተሳለጠ ንግድ ወደሚጨበጥ ሀገራዊ ተስፋ” በሚል መሪ ቃል የዓመቱ ስኬታችን ትሩፋት በሆነው የጥራት መንደር እየተካሄ ነው፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)
"የሃገራችንን የንግድ ስራ ዘመኑን የዋጀ፣ ቀላል፣ ተደራሽና የተሳለጠ ከማድረግ አንጻር በበጀት ዓመቱ መሰረት የጣልንባቸውን ስኬቶች አስመዝግበናል" ብለዋል በመክፈቻ ንግግራቸው፡፡
አያይዘውም "የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥን በማሳደግ በሀገር አቀፍ ደረጃ 2,857,907 በኦንላይን ለመስጠት አቅደን 3,025,767 አከናውነናል። አፈፃፀሙ 106 በመቶ ነው፡፡ ይህም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት አፈፃፀም (2,316,308) ጋር ሲነፃፀር የ709,459 (23.44%) ብልጫ እንዳለው ገልፀዋል ክቡር ሚኒስትሩ ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የድህረ ፍቃድ ኢንስፔክሽን 2,890,600 ለማከናወን አቅደን 3,117,920 (108%) ማከናወን ተችሏል፡፡ የቅዳሜና እሁድ ግብይት ማዕከላትን ከማስፋፋት ረገድ ቀደም ሲል ከነበረበት 1,066 በ2017 በጀት ዓመት 1,300 ለማድረስ አቅደን 571 አዳዲስ ገበያዎችን በመክፈት 1,567 (244%) ደርሷል፡፡
ከጠቅላላው የወጪ ንግድ 5.15 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅደን 8.3 (161.33%) ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማሳካት ተችሏል፡፡ ይህም ከ2016 በጀት አመት ከተገኘው 3.71 ቢሊዮን ጋር ሲነፃፀር 4.59 በሊዮን ዶላር (123.78%) ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና ባለብዙ ወገን የንግድ ትስስር ረገድ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ ብሄራዊ የትግበራ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ ሆኗል፡፡
የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር ሂደት ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ሂደቱን በስኬት ለመቋጨት በበጀት ዓመቱ ሁኔታ ቀያሪ ስራ ተሰርቷል፡፡ 5ኛውን የስራ ቡድን ስብሰባ እ.ኤ.አ በማርች 19 ቀን 2025 በተሳካ መልኩ ካሄዷል፡፡ መስከረም አጋማሽ ለሚካሄደው 6ኛው የስራ ቡድን ስብሰባም የተሟላ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡
በመጨረሻም ዓለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት መሠረተ ልማቶችን አንድ ላይ አካቶ የያዘው ብሔራዊ የጥራት መንደር ተመርቆ ዘርፈ በዙ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ አንዱ አካል የሆነው ኢ-ኮመርስ በዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ደረጃ ተቋቁሞ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያስገቡ ስራዎችን አከናውነናል ብለዋል ሚኒስትሩ ዶክተር ካሳሁን ጎፌ፡፡
በጉባኤው ላይ ሀገራዊ የንግድ ዘርፍና የክልል ንግድ ቢሮዎች የ2017 በጀት ዓመት ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
ለተጨማሪና ትኩስ መረጃዎች የዲጂታል ሚዲያ ገፆቻችንን ይከተሉ!
ፌስ ቡክ፣ BGRS- Trade and Market Development Bureau, https://www.facebook.com/share/p/14oGC7XCvp/
ቴሌግራም ቻናል፤ BGRS- Trade and Market Development Bureau, Link,
https://www.facebook.com/share/19B2tCiJ4f/
ኢሜይል፣ bgrstmd፧@gmail.com
ሞባይል፣+251980248854
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments