በኦሮሚያ ምርታማነትን ለማሳደግና ገበያውን ለማረጋጋት የተሰሩ ስራዎች የሚያኮሩ ነው - ዶ/ር አብዱልሀኪም ሙሉ
በኦሮሚያ ምርታማነትን ለማሳደግና ገበያውን ለማረጋጋት የተሰሩ ስራዎች የሚያኮሩ ነው - ዶ/ር አብዱልሀኪም ሙሉ
የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ ያዘጋጀው ሁለተኛው የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽን በኦሮሞ የባህል ማዕከል ተከፍቷል፡፡
ኤግዚቢሽኑን የከፈቱት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፣ ገበያው እንዲረጋጋ፣ የኑሮ ውድነቱም እንዲቀንስ የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት መድረኮች ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ነው ብለዋል። መድረኩ ተኪ ምርትን በማበረታታትና ወጪ ምርትን በማሳደግ ረገድ ትልቃ ፋይዳ አለው ነው ያሉት።
የንግድ ሣምንት ፋይዳው ግንዛቤ በመፍጠር የሀገር ውስጥ ምርቶችን በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ጥገኝነትንና ተጋላጭነትን ለማሸነፍ ይረዳል
በኦሮሚያ ምርታማነትን ለማሳደግና ገበያውን ለማረጋጋት የተሰሩ ስራዎች የሚያኮሩ መሆናቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ኃላፊ የሺ ጂማ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ሳምንቱ የኦሮሚያ ክልል የንግድ ሳምንት ተብሎ መሰየሙን ጠቅሰው፣ ክልሉን ከሌሎች ክልሎች ጋር በንግድ ለማስተሳሰርና ልምድ እንዲለዋወጡ አላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ የሚመረቱ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በሚገባ ለማስተዋወቅ የሚያግዝ መድረክ ስለመሆኑም ነው የተናገሩት።
በባዛሩና በኤግዚቢሽኑ ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች ምርቶቻቸውን ለዕይታ አቅርበዋል።
በኤግዚቢሽኑ ላይ ከቀረቡት ለዓለም ገበያ ከሚቀርቡ የግብርናና የማዕድን ምርቶች መካከል የቁም ከብቶችን ጨምሮ ቡና፣ ሰሊጥ፣ ማር እና ማሾ የተለያዩ የቦለቄ ዝርያዎች እና የአምቦ ድንጋይ ምርቶች የሚጠቀሱ ናቸው።
ለሀገር ውስጥ ገበያ ከሚቀርቡት ምርቶች ውስጥ ደግሞ የሰብልና የጥራጥሬ ምርቶች፣ ወተትና የወተት ተዋጽኦ፣ የስንዴ ዱቄት፣ የምግብ ዘይትና ሌሎች እሴት የተጨመረባቸው የፋብሪካ ውጤቶች ይጠቀሳሉ።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments