ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት ላይ ትኩ...

image description
- In 2ኛው ከተማ ዓቀፍ "የኢትዮጵያን ይግዙ"    0

ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት ላይ ትኩረት ተደርጓል፦

ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት ላይ ትኩረት ተደርጓል፦

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

********************

ለዘመን መለወጫ ለነዋሪው ምቹ የገበያ አማራጭ በመፍጠር የምርት ፍላጎት እና አቅርቦትን ለማጣጣም እየተሰራ ነው ሲል የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በመስከረም ወር አዲስ ዓመትን ጨምሮ በርካታ በዓላት እንደሚከበሩ አስታውሰዋል። ለነዋሪው ምቹ እና ተመጣጣኝ የግብይት ሥርዓት ለመፍጠር እንዲሁም የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የቁም እንስሳት፣ ሰብል፣ የእንስሳት ተዋጽዖዎች፣ አልባሳት፣የአትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም ሌሎች ምርቶችን ላይ የዋጋ ንረትም ሆነ እጥረት እንዳይፈጠር የከተማ አስተዳደሩ አቅርቦት ላይ እንሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በከተማዋ ከ500 ሺ በላይ ነጋዴዎች መኖራቸውን አንስተው፤ ከ95 በመቶ የሚሆኑት የንግድ ሕጉን ተከትለው እንደሚሰሩ ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡

ያለአግባብ ዋጋ የሚጨምሩና ምርት የሚደብቁ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱንም አስታውቀዋል።

በተጨማሪ ከነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 5 ቀን ድረስ በተለያዩ ቦታዎች በርካታ ባዛሮች እንደሚዘጋጁም ጠቁመዋል፡፡

ይህም ሸማቹ በአቅራቢያው እንዲሸምት እንደሚያግዝም ነው የተናገሩት።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments