የኢትዮጵያን ይግዙ 2ኛ ዓመት የንግድ ሳምንት ኢ...

image description
- In 2ኛው ከተማ ዓቀፍ "የኢትዮጵያን ይግዙ"    0

የኢትዮጵያን ይግዙ 2ኛ ዓመት የንግድ ሳምንት ኢግዚቪሽንና ባዛር የዝግጅት ስራዎች የተጠናቀቁ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያን ይግዙ 2ኛ ዓመት የንግድ ሳምንት ኢግዚቪሽንና ባዛር የዝግጅት ስራዎች የተጠናቀቁ መሆኑ ተገለፀ፡፡

====================

አዲስ አበባ፡ ነሀሴ 21/2017 ዓ.ም

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አዘጋጅነት የሚካሄደው የኢትዮጵያን ይግዙ 2ኛ ዓመት የንግድ ሳምንት ኢግዚቪሽንና ባዛር ደማቅና አሳታፊ በሆነ ሁኔታ ላማካሄድ የዝግጅት ስራዎች የተጠናቀቁ መሆኑን በሚኒስቴሩ የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚነስትር ዴኤታ ዶ/ር አብዱልሃኪም ሙሉ ገለፁ፡፡

ዶ/ር አብዱልሃኪም ሙሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁሉንም ክልሎች፣ ሴክተር መ/ቤቶችን፣የንግዱ ማህበረሰብንና ሸማቾችን ባሳተፈ ሁኔታ ከነሃሴ 24-29/2017 ዓ.ም ድረስ የሚካሄደውን የኢትዮጵያን ይግዙ 2ኛ ዓመት የንግድ ሳምንት ኢግዚቪሽንና ባዛር ዝግጅት አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ባለፉት ሳምንታት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የንግድ ሳምንት ኢግዚቪሽንና ባዛር በማካሄድ በክልሎች ያለውን እምቅ አቅም፣ የምርትና አገልግሎቶች ትውውቅና ግብይት ሲካሄድ የነበረ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው በሀገር አቀፍ ደረጃ በጥራት መንደር እንደሚካሄድና ሁሉም አይነት የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲሁም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተደራጀ ሁኔታ በማቅረብ የሀገራችንን የማምረት አቅምና ፀጋ በስፋት ለማስተዋወቅ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡

የእግዚቪሽንና ባዛሩ ዓላማ የሀገራችንን ምርትና አገልግሎቶችን በስፋት ለማስተዋወቅ፣ዜጋው የሀገራችንን ምርቶች እንዲገዛና እንዲጠቀም ለማድረግ፣ የኢትዮጵያን ምርቶች የጥራት ደረጃ ሁሉም እንዲረዳ ለማድረግ፣በሀገር ምርት መጠቀምን ለመለማመድና ባህል ለማድረግ እንደሆነ ዶ/ር አብዱልሃኪም ገልፀዋል፡፡

ባለፉት የለውጥ አመታት በሀገራችን ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ አዳዲስ የማምረት ሃሳቦችና የአሰራር ማሻቻዎችን ተግባራዊ በማድረግ በክረምትና በበጋ በመጠቀም የማምረት አቅማችን በአይነት፣ በጥራትና በመጠን እያደገ መጥቷል ያሉት ዶ/ር አብዱልሃኪም በሀገር ውስጥ የተመረቱትን የመግዛትና የመጠቀም እንዲሁም የገበያ ትስስር በመፍጠር አምራቾችና ሸማቾች ተገናኝተው ምርቶቻቸውን የሚያስተዋዉቁበት በተመጣጣኝ ዋጋ ግብይት የሚፈፀምበት የገበያ ትስስር የሚፈጠርበት እንደዚህ አይነት ኢግዚቪሽንና ባዛር ማመቻቸት አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments