ቢሮው የንግድ ድርጅቶች የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር ስራ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ለማስቻል ባበለጸገው አዲስ ቴክኖሎጂ ዙርያ ስልጠና ሰጠ፤
ቢሮው የንግድ ድርጅቶች የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር ስራ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ለማስቻል ባበለጸገው አዲስ ቴክኖሎጂ ዙርያ ስልጠና ሰጠ፤
============+++===========
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ ነሃሴ 27/2017 ዓ.ም.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የንግድ ድርጅቶች የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር ስራ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ለማስቻል፣ ባበለጸገው አዲስ ቴክኖሎጂ ዙርያ ለከተማ፣ ክ/ከተማና ወረዳ የንግድ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ከዚህ ቀደም በቦሌና ጉለሌ ክ/ከተሞች በሙከራ(Pilot) ፕሮጀክት ደረጃ ሲተገበር የቆየው ይህ የበር ለበር ቁጥጥር የonline ቴክኖሎጂ በሁሉም ክ/ከተሞች በሙላት መተግበሩ፣ በከተማችን ዘመኑን የዋጀ፣ ፍትሃዊና ተወዳዳሪ የንግድ ስርዓት እንዲሰፍን ከማድረጉም ባሻገር፣ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓታችንን በማዘመን በዘርፉ የሚስተዋለውን ብልሹ አሰራር እንደሚቀንሰው ገልጸዋል።
ስልጠናው በሶስት ክላስተተሮች ተከፋፍሎ የተሰጠ ሲሆን፤
1ኛ. በልደታ ክላስተር የስልጠናው ቦታ ልደታ ክፍለ ከተማ ሲሆን፣ የአዲስ ከተማ፣ ልደታ እና ቂርቆስ ክ/ከተሞች የክ/ከተማና ወረዳ አመራሮችና የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ቡድን ባለሙያዎች፤
2ኛ. በየካ ክላስተር የስልጠናው ቦታ የካ ክፍለ ከተማ ሲሆን፣ የለሚኩራ፣ የካ እና አራዳ ክ/ከተሞች የክ/ከተማና ወረዳ አመራሮችና የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ቡድን ባለሙያዎች፤
3ኛ. በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክላስተር የስልጠናው ቦታ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሲሆን፣ የአቃቂ ቃሊቲ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶና ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተሞች የክ/ከተማና ወረዳ አመራሮችና የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ቡድን ባለሙያዎች በስልጠናው ተሳትፈዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments