ቢሮው በመጪው መስከረም ወር በሚከበሩ በዓላት በ...

image description
- In ንግደረ    0

ቢሮው በመጪው መስከረም ወር በሚከበሩ በዓላት በከተማችን የተረጋጋ ግብይት እንዲኖር እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ዙርያ ለመገናኛ ብዙሃን ገለጻ አደረገ፤

ቢሮው በመጪው መስከረም ወር በሚከበሩ በዓላት በከተማችን የተረጋጋ ግብይት እንዲኖር እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ዙርያ ለመገናኛ ብዙሃን ገለጻ አደረገ፤

===================

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በመጪው የመስከረም ወር በሚከበሩ በዓላት በከተመችን የተረጋጋ ግብይት እንዲኖር እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ዙርያ ለመገናኛ ብዙሃን ገለጻ አድርጓል፡፡ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በመስከረም ወር ለሚከበሩ በዓላት በከተማችን በቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖር መሰራቱን አሳውቀዋል። በአዲሱ ዓመት የሚኖረውን የምርቶች አቅርቦትና ቁጥጥርን በሚመለከት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ የሰጡት ወ/ሮ ሀቢባ፣ ለ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ከማዕከል እስከ ወረዳ የአቅርቦት እና የህገወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ የቅድመ ዝግጅት ስራ መስራቱን አስታውቀዋል። በተሰራው የቅድመ ዝግጅት ስራም መንግስት በሚያስተዳድራቸው በ10 የገበያ ማዕከላት፣ በ219 የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እና በ20 ባዛሮች ላይ የተለያዩ ምርቶች በስፋት መቅረባቸውን ተናግረዋል። ለዘንድሮው የአዲስ ዓመት በዓል የቀረበው ምርት ባለፈው ዓመት ከቀረበው ጋር ሲነጻጸር የ25 በመቶ ብልጫ እንዳለውም ገልጸዋል።

በገበያ ማዕከለት የቀረቡት ምርቶች 30 በመቶ ሲሆኑ፤ ቀሪው 70 በመቶ በነጻ ገበያው የሚቀርብ መሆኑን አመላክተዋል። ከምርት አቅርቦት በተጨማሪም መጋዘን ውስጥ ክምችት እንዳይኖር ክትትልና ቁጥጥር ይደረጋል ብለዋል።

በህገወጥ ደላሎች፣ በዓድ ነገር በሚቀላቅሉ፣ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶችን ወደ ገበያ በሚያስገቡና ዋጋ በሚጨምሩ ነገዴዎች ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት

https://www.facebook.com/profile.php?id=100069351701097

https://t.me/Addisababatradebureau

https://vm.tiktok.com/ZMB4AxNvr/

https://youtube.com/@addisababatradebureau-s2d..


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments