በእመርታ እና ማንሰራራት የታጀበዉ ህዝባዊ በዓላት በጋራ እናክብር"
በእመርታ እና ማንሰራራት የታጀበዉ ህዝባዊ በዓላት በጋራ እናክብር"
===============================
አዲስአበባ፡-መስከረም9ቀን2018ዓ/ም
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የመስቀልና ኢሬቻን በአላቶችን በእመርታ በማንሰራራት የታጀበና በጋራ ለማክበር ከቢሮ ሰራተኞቹ ጋር ውይይት አደረገ ፡፡
የቢሮው ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ገመቹ በአላቶቹን ስናከብር በእንግዳ ተቀባይነት ፤በጨዋነት መሆን እንደሚገባው እና አላስፈላጊ ነገሮች እንዳይከሰት የራሳችሁን ሚና መወጣት እንደሚገባ በየደረጃው ያሉ የንግድ አደረጃጀቶች ጋር በመባበር መስራት እንደሚገባ በውይይቱ ገልፀዋል፡፡
የቢሮው የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ሚኤሶ ለውይይት የቀረበውን ሰነድ አቅርበው በአላቶችን ስናከብር የበአሉን ትውፊት ብቻ በማሰብ መሆን እንደሚገባ እና ከተስፋ ብርሀን ወደ ሚጨበጥ ብርሃን እንደርሳለን በሚል ከሰራተኞታቸው ጋር ውይይት አድርገዋል
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments