ቢሮው ከባለድርሻ አካላት የ2018ዓ/ም የመስቀል/ደመራ እና የኢሬቻ በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀ የኢዚቢሽን ባዛር ማስፈፀሚያ እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
ቢሮው ከባለድርሻ አካላት የ2018ዓ/ም የመስቀል/ደመራ እና የኢሬቻ በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀ የኢዚቢሽን ባዛር ማስፈፀሚያ እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
===================================================
አዲስ አበባ ፡- መስከረም 9ቀን 2018ዓ/ም
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከባለድርሻ አካላት የ2018ዓ/ም የመስቀል/ደመራ እና የኢሬቻ በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀ የኢዚቢሽን ባዛር ማስፈፀሚያ እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
የቢሮው ንግድና ግብይት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሀ ጥበቡ የባዛሩን ዕቅድ ዙሪያ አስቻይ ሁኔታዎች፤በስጋት ደረጃ ሊታዩ የሚችሉ እና የነጋዴ ማህበረሰብ ሞብላይዜሽንና ባዛር ኮሚቴዎችንሌሎች ኮሚቴዎችን ስራዎች ለመወያያ በሚመች መልከ ሰነድ አቅርበዋል፡፡
በተያያዘም እነዚህን ባዕላቶች ወደ ኢኮነሚያዊ ስራዎች መቀየር እንደሚገባና ክፍለ ከተሞች በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል
በመጨረሻም የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በዓሉ ዋና ነገር እብረተሰቡ ሁለቱንም ባዕላቶች ወዶ ያለምንም ችግር እንዲያከብራቸው እና የአትክልት ፍራፍሬ ፤የሰብል ፤እንዲሁም የአልባሳት የጌጣጌጥ ፤የሚበላ የሚጠጣ ካለምን እጥረት መቅረብ እንደሚገባ አሳስበው የንግድ ሱቅ የሚዘጉ ካሉ እርምጃ እንደሚወሰድም ገልፀዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments