"ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደታደሰ ቁመና!"...

image description
- In 2ኛው ከተማ ዓቀፍ "የኢትዮጵያን ይግዙ"    0

"ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደታደሰ ቁመና!" በሚል መሪ ርዕስ የቢሮው ከፍተኛ አመራርና አጠቃላይ ሰራተኞች ውይይት አካሄዱ፤

"ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደታደሰ ቁመና!" በሚል መሪ ርዕስ የቢሮው ከፍተኛ አመራርና አጠቃላይ ሰራተኞች ውይይት አካሄዱ፤

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ መስከረም 27/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አመራርና አጠቃላይ ሰራተኞች "ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደታደሰ ቁመና!" በሚል ርዕሰ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ውይይት አካሂደዋል።

የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት በንግድ ቢሮ የግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ፍሰሃ ጥበቡ አገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በቀጠናችን፣ በአህጉር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከነበረችበት ኩስመና ተላቃ ወደታደሰና ወደተሻለ ቁመና እንድታድግና ወደ ቀደመ ግዝፈቷ እንድትመለስ በመንግስትና በህዝቡ ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ይህንን ለማሳካትም ድልን በማላቅ፣ የዘመናት ኩስምናን ለመቋጨት እንዲቻል፣ የሥነ-ልቦና የበላይነት በመጨበጥና ልዩነቶችን በመፍታት በቀይ ባህር ላይ ያለንን ተፈጥሯዊና ታራካዊ መብት ለማስመለሰ በጋራ መስራት ይኖርብናል"ብለዋል። ለዚህም ከባንዳና ባዳጋር ባለማበር አገርን ለማበልጸግ የሚደረገውን ጥረት መደገፍ ይኖርብናል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የውይይቱ ዋና ዓላማ አገራችን ኢትዮጵያ ከሁለት ውሃዎች (ከአባይና ቀይ-ባህር) በራቀችና በቀረበች ቁጥር ያጣቻቸውና የምታገኛቸውን ጥቅሞች አንስተው፣ ከአምስቱ ከለባት(ከባንዳና ባዳዎች) አገርን ለመጠበቅ እንደ መንግሥት ሰራተኛ ከኛ ምን ይጠበቃል የሚለውን አብራርተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ሰራተኞች በበኩላቸው አገራችን ኢትዮጵያ ወደተሻለ ቁመና እንድትደርስ በሁለቱ ውሃዎች ላይ ያላትን ባለቤትነትና መብት ማስከበር አስፈላጊ መሆኑን አንስተው፣ ከባንዳና ባዳ አገርን ለመከላከል መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በውይይቱ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ዓለም ከአንድ ዋልታ ወደ ብዝሃ ዋልታ እየሄደች መሆኑን አንስተዋል። ከመክሰም በኋላ ወደ ዳግም ጦርነት ለመመለስ የሚፈልጉትን በመግራት፣ በዚህ በብዝሃ ዋልታ ዘመን ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌታዊ ብልጽግና እንድትሻገር ለማድረግና በውስጣችን ያሉ ባንዳዎችን በመለየትና በማረም ከባዳዎች አገርን ለመከላከል፤ ድልን በማላቅ የዘመናት ጥፋትን ለመቋጨትና የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ሥነ-ልቦና የበላይነት ለመጨበጥ ልዩነቶችን በመፍታት በቀይ-ባህር ላይ ያለንን ተፈጥሯዊና ታራካዊ መብት ለማስመለሰ እንተጋለን ብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments