የቢሮው ፕሮሰስ ካውንስል በ2018 በጀት ዓመት የመጀመርያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፤
የቢሮው ፕሮሰስ ካውንስል በ2018 በጀት ዓመት የመጀመርያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፤
#########+++##########
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ መስከረም 28/2018 ዓ.ም.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ፕሮሰስ ካውንስል በ2018 በጀት ዓመት የመጀመርያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አከናውኗል፡፡ የቢሮውን የመጀመርያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የቢሮው እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መለሰ ባህሩ ሲሆኑ፤ በግምገማው ላይ የቢሮው ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በበጀት ዓመቱ ቢሮው ያቀዳቸውን ተግባራት ለማሳካት በየጊዜው የሚደረግ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፤ ከተማችን ዘመናዊ፣ ፍትሃዊና ተወዳዳሪ የንግድ ስርዓት የሰፈነባት የአፍሪካ የንግድ ከተማ እንድትሆን ለማስቻልና ፈጣንና ቀልጣፋ የንግድ ሥርዓትን በማስፈን የከተማችንን ነዋሪ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ በተያዘው በጀት ዓመት በንግዱ ዘርፍ የሚሰተዋሉ ችግሮች ለመቅረፍ፤ በተለይም በንግድና ግብይት ስርዓቱ ውስጥ የሚታዩትን ህገ-ወጥ የንግድ ተግባራትን በመከላከል ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣትና የንግዱንና የሸማቹን ማህበረሰብ ፍትሃዊ የሀብት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደትግበራ መግባቱንና ባለፉት ሦስት ወራትም ይህንን ለማሳካት መሰራቱን ገልጸዋል፡፡
በተጫመሪም ወ/ሮ ሀቢባ ቢሮው የበጀት ዓመቱን እቅድ እንዲያሳካና የንግዱ ማህበረሰብ በፍትሃዊነት የሚሰራበት ምቹ ምህዳር እንዲፈጠር፤ በየደረጃው ያለ አመራርና ፈጻሚ በበጀት ዓመቱ እቅድ ትግበራ ወቅት የአገልግሎት አሰጣጡን ከብልሹ አሰራር የጸዳ እንዲሆን በማድረግና በማቀላጠፍ፣ የሚስተዋሉ ጠንካራ ጎኖችን ማጠናከር፣ ደካማ ጎኖችን በመለየት ማረም አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ለዚህም የሚስተዋሉ የአመለካከት፣ የክህሎትና የግብዓት ክፍተቶችን በመለየት መፍታት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069351701097
https://t.me/Addisababatradebureau
https://vm.tiktok.com/ZMB4AxNvr/
https://youtube.com/@addisababatradebureau-s2d...
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments