ቢሮው ከከተማ እስከ ወረዳ ከሚገኘው መዋቅሩጋር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመርያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፤
ቢሮው ከከተማ እስከ ወረዳ ከሚገኘው መዋቅሩጋር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመርያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፤
#########+++##########
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከከተማ እስከ ወረዳ ከሚገኘው መዋቅርጋር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመርያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል፡፡ የቢሮው አጠቃላይ አመራርና ሰራተኞች፣ የ11ዱም ክ/ከተሞችና የ119 ዱም ወረዳዎች ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በጉለሌ ክ/ከተማ መስብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል። የቢሮው እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መለሰ ባህሩ የመጀመርያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ያቀረቡ ሲሆኑ፤ በክ/ከተሞች የተካሄደ የመጀመርያ ሩብ ዓመት የክትትልና ድጋፍ ስራዎች ግብረ-መልስን የቢሮው የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ አብዮት ቱሉ አቅርበዋል።
የግምገማው ተሳታፊዎች በየጊዜው የሚደረግ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፤ የተለያዩ ሃሳቦችን፣ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን ለቤቱ አንስተዋል።
ከተሳታፊዎች ለቀረቡት ሃሳቦች፣ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ማብራርያና ምላሽ የሰጡ ሲሆን፤ ቢሮው አንጋፋ እንደመሆኑ በበጀት ዓመቱ ያቀዳቸውን ተግባራት ለማሳካት እንዲቻልና ከተማችን ዘመናዊ፣ ፍትሃዊና ተወዳዳሪ የንግድ ስርዓት የሰፈነባት የአፍሪካ የንግድ ከተማ እንድትሆን በማስቻል ፈጣንና ቀልጣፋ የንግድ ሥርዓትን በማስፈን፣ የከተማችንን ነዋሪ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጥናት ታግዞ ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በመሰረታዊ ፍጆታ ሸቀጦች ስርጭት ላይ የሚሰተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍና ህገ-ወጥ የንግድ ተግባራትን በመከላከል ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣትና የሸማቹን ማህበረሰብ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ባለፉት ሦስት ወራት በከተማችን ወደ ንግዱ ስርዓት ለሚቀላቀሉ ነጋዴዎች የአንድ ማዕከል የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጡን ቀላልና ዘመናዊ ከማድረግ አኳ፣ እንዲሁም የፈቃድ እድሳት አገልግሎቶችን ከማዘመን አንጻር የተከናወኑት ተግባራት ይበል የሚያሰኙ መሆናቸውን ገልጸው ይህም በቀጣዮቹ ወራት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል፡፡ የመሰረታዊ የፍጆታ የግብርና ምርቶች በዘላቂነት ወደ ከተማችን በስፋት እንዲገቡ ከማድረግና ግብይቱንም በዘመናዊ መንገድ ከመምራት አኳያ በከተማችን የመግቢያ በሮች ላይ በሚገኙ አራት ሁለገብ የግብርናና የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ማከፋፈያ የገበያ ማዕከላት ምርቶች እንዲቀርቡ ለማድረግና የግብይት ሰንሰለቱን ለማሳጠር መሰራቱን አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ለማጠናከርና ለማስፋት ሊሰራ ይገባል ብለዋል። ባለፉት ሦስት ወራት በተዘጋጁ ኤግዚቢሺንና ባዛሮች ላይ ለአዲስ ዓመት፣ ለመስቀልና ለኢሬቻ በዓላት የግብርና ምርቶችን በቀጥታ ከአርሶ አደሩና ከአምራች ኢንዱስትሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ እንዲቀርብ መደረጉን አንስተዋል፡፡ በሩብ ዓመቱ የገበያ ዋጋ መረጃ የመሰብሰብ፣ የመተንተን እና የማቀነባበር ተግባራትን መከናወናቸውንም ገልጸዋል፡፡
በቢሮው የንግድ ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ስመኘው ተሾመ ባሳለፍነው የመጀመርያው ሩብ ዓመት የተጀመረው የበር ለበር የኦንላይን ቁጥጥር ቴክኖሎጂ በሁሉም ክ/ከተሞች 100% እንዲተገበር የማድረግ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፣ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች፣ በPPP በተገነቡ የዳቦ ቤቶች፣ በመንግስት በተገነቡ የገበያ ማዕከላትና በነዳጅ ማደያዎች ላይ ጥብቅ የክትልና ቁጥጥር ስራ መጠናከር አለበት ብለዋል፡፡ የንግድ ተቋማት ላይ የበርለበር ቁጥጥር በማድረግ ጥፋተኞችን መለየት፣ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድና ወደ ህጋዊነት እንዲመለሱ መደረግ፣ የልኬት መሳሪያዎችን ትክክለኝነት ማረጋገጥና ኮንትሮባንድ ላይ የሚሰሩ ስራዎች መልካም ነው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። የምሽት ንግድ ቁጥጥሩም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
በመጨረሻም ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ቢሮው የበጀት ዓመቱን እቅድ እንዲያሳካና የንግዱ ማህበረሰብ በፍትሃዊነት የሚሰራበት ምቹ ምህዳር እንዲፈጠር፤ በየደረጃው ያለ አመራርና ፈጻሚ በበጀት ዓመቱ እቅድ ትግበራ ወቅት የአገልግሎት አሰጣጡን ከብልሹ አሰራር የጸዳ እንዲሆን በማድረግና በማቀላጠፍ፣ የሚስተዋሉ ጠንካራ ጎኖችን ማጠናከር፣ ደካማ ጎኖችን በመለየት ማረም አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ለዚህም የሚስተዋሉ የአመለካከት፣ የክህሎትና የግብዓት ክፍተቶችን በመለየት መፍታት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069351701097
https://t.me/Addisababatradebureau
https://vm.tiktok.com/ZMB4AxNvr/
https://youtube.com/@addisababatradebureau-s2d.
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments