ቢሮው በሩብ አመቱ የዕቅድ አፈፃፀም ላይ ከንግድ ኢንዱስትሪ ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር ዉይይት አካሄደ!
ቢሮው በሩብ አመቱ የዕቅድ አፈፃፀም ላይ ከንግድ ኢንዱስትሪ ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር ዉይይት አካሄደ!
=============+++==========
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፤ ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በንግድ ቢሮ ተገኝቶ በበጀት ዓመቱ የመጀመርያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ከቢሮው የማኔጅሜንት አባላትጋር ጥልቅ ውይይት ያካሄደ ሲሆን፤ በውይይቱ የቢሮው የ1ኛ ሩብ ዓመት ዋና ዋና ተግባራት(KPI) አፈጻጸም ከፍተኛ መሆናቸው ተመላክቷል።
መድረኩን የመሩት የንግድ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ክብርት ዶ/ር አጋረደች ጀማነህ ቢሮው የከተማችንን ነዋሪ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ፍትሃዊና ተወዳዳሪ የንግድ ስርዓት ለመዘርጋት የጀመረው ጉዞ በቀጣዮቹ ወራት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
የንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው ቢሮው በከተማችን የሚካሄደው የንግድ ሥርዓት ዘመኑን የዋጀ፣ ፍትሃዊና በውድድር ላይ የተመሰረት እንዲሆን በማድረግ፤ አዲስ አበባ የአፍሪካ ግንባር ቀደም የንግድ ከተማ እንድትሆን እየተሰሩ ያሉ ተግባራት በቀጣዮቹ ወራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
በመጨረሻም በቀረበው የ1ኛ ሩብ ዓመት ሪፓርት ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዶ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል።
ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069351701097
https://t.me/Addisababatradebureau
https://vm.tiktok.com/ZMB4AxNvr/
https://youtube.com/@addisababatradebureau-s2d...
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments