በከተማዋ ውስጥ ቀጣይነት ያለው የተረጋጋ ግብይት...

image description
- In ንግደረ    0

በከተማዋ ውስጥ ቀጣይነት ያለው የተረጋጋ ግብይት እንዲኖር በቀጣይነት በሚሰሩ ስራዎች ላይ የገበያ ማረጋጋት፣ የንግድ ቁጥጥርና አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ታምርት ግብረ ሀይል አባላት ውይይት አድርገዋል፡፡

በከተማዋ ውስጥ ቀጣይነት ያለው የተረጋጋ ግብይት እንዲኖር በቀጣይነት በሚሰሩ ስራዎች ላይ የገበያ ማረጋጋት፣ የንግድ ቁጥጥርና አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ታምርት ግብረ ሀይል አባላት ውይይት አድርገዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት በከተማዋ የተረጋጋ ግብይት እንዲኖርና የህበረተሰቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ ከማእከል እስከ ወረዳ የተቋቋመው የገበያ ማረጋጋት፣ የንግድ ቁጥጥርና አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ታምርት ግብረ ሀይል በሰራው ስራ ለሌሎች ክልሎች አርያ የሚሆን ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

በባለፈው በጀት ዓመት ገበያውን ለማረጋጋት ግብረ ሀይሉ እቅድን መሰረት በማድረግ የኢ መደበኛንና የምሽት ንግድን በመቆጣጠር፣ የህግ የበላይነትን ለማስከበር ከጸጥታ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር፣ ህገወጥ የፍጆታ ምርቶች ዝውውርን በመቆጣጠር ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ቁርጠኛ አመራር በመስጠት ተጨባጭ ስራ መሰራቱን የተከበሩ አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ገበያውን ለማረጋጋት አቅርቦትን በማሳደግ፣ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ትስስር በማድረግ እና ህግን በማስከበር ግብረ ሃይሉ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት በትኩረት እንዲሰሩ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ አሳስበዋል፡፡

ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት

https://www.facebook.com/profile.php?id=100069351701097

https://t.me/Addisababatradebureau

https://vm.tiktok.com/ZMB4AxNvr/

https://youtube.com/@addisababatradebureau-s2d


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments