በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የ90...

image description
- In ንግደረ    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የ90 ቀናት እቅድ አፈፃፀም የንግድ ተቋም እና ከባለድርሻ አባለት ጋር ውይይት ተካሄደ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የ90 ቀናት እቅድ አፈፃፀም የንግድ ተቋም እና ከባለድርሻ አባለት ጋር ውይይት ተካሄደ

‎===========================

‎የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ‎በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የ90 ቀናት እቅድ አፈፃፀም የንግድ ተቋም እና ከባለድርሻ አባለት ጋር ውይይት አካሄደ።

‎የእቅድ እና ውይይት ያስጀመሩት የቢሮው የግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋይ ደበለ መጀመሪያ የውይይት ዓላማ በዋና ዋና ግቦች በማሳካት ረገድ ቢሮው ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸው በተለይም በምርት አቅርቦት እና በግብይት ዘርፍ ሁሉንም የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በአገባቡ በመምራት እና የምርት አቅርቦት እጥረት እናዳይኖር በማድረግ ረገድ የተሳካ መሆኑን ገልፀዋል

‎በዛሬው ዕለት በቢሮው የንግድ ግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መከታው አዳፍሬ የ90 ቀናት እቅድ በጥሩ ሁኔታ አቅርበዋል።

‎አክሎም የንግድ ቢሮ የንግድና ሬጉላቶሪ ኢንስፔክሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ስመኘው ተሾመ ቁጥጥሩ የእሁድ ገበያ እና የገበያ ማዕከላትን ጨምሮ የህገወጥ ንግድ ላይ ቁጥጥር በደንብ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።

‎በመጨረሻም ከመድረክ በተነሳ ሀሳቦች ላይ ምላሽ ተስጥቶበት ተጠናቋል።

‎ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት

https://www.facebook.com/profile.php?id=100069351701097

https://t.me/Addisababatradebureau

https://vm.tiktok.com/ZMB4AxNvr/

https://youtube.com/@addisababatradebureau-s2d...


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments