ቢሮው የቁም እንስሳት የገበያ ማዕከላት የ4 ወ...

image description
- In ንግደረ    0

ቢሮው የቁም እንስሳት የገበያ ማዕከላት የ4 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማን ከባለድርሻ አካላትጋር አካሄደ፤

ቢሮው የቁም እንስሳት የገበያ ማዕከላት የ4 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማን ከባለድርሻ አካላትጋር አካሄደ፤

‎==========================

‎አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ ህዳር 4/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የቁም እንስሳት የገበያ ማእከላት የ4 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ከአምስቱ ክ/ከተሞች(ጉለሌ፣ የካ፣ አዲስ ከተማ፣ አቃቂ ቃሊቲና ንፋስ ስልክ ላፍቶ) ንግድ ጽ/ቤቶች ኃላፊዎችና የቁም እንስሳት ማህበራት ጋር ገምግሟል።

‎ግምገማውን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ "የቁም እንስሳት የገበያ ማእከላትን ዘመናዊ ለማድረግ ከተማ አስተዳደሩ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፣ በማዕከላቱ የሚስተዋሉ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለመቀነስ ለቁም እንስሳት ነጋዴዎች ዩኒፎርም ማልበስና ባጅ ማዘጋጀት ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል።

‎የቁም እንስሳት የገበያ ማእከላት የ2018 በጀት ዓመት የ4 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደበሬ ዲንሳ አቅርበዋል።

‎በመጨረሻም የቢሮ ኃላፊዋ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በተነሱት ሀሳቦች ላይ በህገወጥ መንገድ የሚነግዱ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊነት ለመመለስ የቁጥጥርና ክትትል ስራው ተጠናክሮ መሰራት ይኖርበታል ብለዋል። አክለውም በንግድ ፈቃድ፣ በዩኒፎርም ልብስና በባጅ የሚለዩ ህጋዊና ዘመናዊ ሆኖ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።

The bureau conducted a 4 month plan implementation evaluation of animal markets with stakeholders;

==========…

See more


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments