ቢሮው የበር ለበር ቴክኖሎጂ ምዝገባ አፈጻጸም የ...

image description
- In ንግደረ    0

ቢሮው የበር ለበር ቴክኖሎጂ ምዝገባ አፈጻጸም የደረሰበት ደረጃን ከክ/ከተሞችና ወረዳዎች ቡድን መሪዎችጋር ገመገመ፤

ቢሮው የበር ለበር ቴክኖሎጂ ምዝገባ አፈጻጸም የደረሰበት ደረጃን ከክ/ከተሞችና ወረዳዎች ቡድን መሪዎችጋር ገመገመ፤

‎==========================

‎አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ ህዳር 4/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የበር ለበር ቴክኖሎጂ ምዝገባ አፈጻጸምን ከክ/ከተሞችና ወረዳዎች ጋር ገምግሟል። ‎ግምገማውን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ስመኘው ተሾመና የቢሮው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ገመቹ ሲሆኑ፤ የበር ለበር ቴክኖሎጂ ምዝገባ አጠቃላይ አፈጻጸሙ በንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ አሰፋ የቀረበ ሲሆን፣ በምዝገባ ሂደት የገጠሙ ተግዳሮቶችና አጠቃላይ የቴክኖሎጂ ምዝገባ ሂደት በተሳታፊዎች ቀርቧል።

አቶ ስመኘው ተሾመ በከተማችን የሚካሄደውን የንግድ ድርጅቶች የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር ተግባርን ዘመናዊ ለማድረግ በቴክኖሎጂ እንዲመዘገብና እንዲታገዝ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንና ለዚህም ምዝገባ መጀመሩን ገልጸው፣ ይሁንና ምዝገባው በታለመለት ጊዜ አለመጠናቀቁንና በፍጥነት መጠናቀቅ እንደሚገባ ገልጸዋል። ‎የቢሮው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ገመቹ የበር ለበር የቴክኖሎጂ ምዝገባው ተጠናክሮ ሊቀጥልና በፍጥነት ሊጠናቀቅ ይኖርበታል ሲሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments