የቢሮው የሠራተኞች መረዳጃ ማህበር ዓመታዊ መደበ...

image description
- In ንግደረ    0

የቢሮው የሠራተኞች መረዳጃ ማህበር ዓመታዊ መደበኛ ጉባኤውን በድምቀት አካሄደ፤

የቢሮው የሠራተኞች መረዳጃ ማህበር ዓመታዊ መደበኛ ጉባኤውን በድምቀት አካሄደ፤

‎==========================

‎አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ ህዳር 6/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የሠራተኞች መረዳጃ ማህበር ዓመታዊ መደበኛ ጉባኤውን በድምቀት አካሂዷል። በጉባኤው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በንግድ ቢሮ የንግድ ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ስመኘው ተሾመ መተሳሰብ፣ መረዳዳትና አብሮነት የኢትዮጵያውያን መገለጫ በመሆኑ በቢሯችን የሚገኘውን የሠራተኞች መረዳጃ ማህበር ማሳደግና ወደላቀ ደረጃ ማድረስ ተገቢ መሆኑን ገልጸው፣ ማህበሩን ሁላችንም ተረባርበን ልናሳድገው ይገባል ብለዋል።

የቢሮው የሰው ሀብት ልማትና ሥራ አመራር ዳይሬክተር የሆኑት

አቶ ዳንኤል ሚኤሳ በበኩላቸው የሠራተኞች መረዳጃ ማህበሩ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ለአባላቱ በደስታም ሆነ በሀዘን ድጋፍ ሲያደርግ የቆየና በማድረግ ላይ የሚገኝ እንደሆነ ተናግረው የእርስ በእርስ መስተጋብርን ለማጠናከር ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የሁላችንም እርብርብ እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ ከቢሮው በዝውውር ወደሌሎች ተቋማት ለተዘዋወሩ የቀድሞ የተቋሙ ተሿሚ አመራሮች፣ በጡረታ ለተገለሉ የቀድሞ የቢሮው ሰራተኞችና በሞት ለተለዩ 1 የቀድሞ የቢሮው ሰራተኛ ቤተሰቦች በመረዳጃ ማህበሩ ስም ስጦታ አበርክቶላቸዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ተቋማዊ አንድነትን ለማጎልበትና የእርስ በእርስ መስተጋብርን ለማጠናከር ሠራተኞች ስጦታዎችን እርስ በእርሳቸው ተለዋውጠዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments