በከተማ ደረጃ በተቋቋመ ግብረሃይል የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር ባለፉት ሦስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትና የቀጣይ ስምንት ወራት ዕቅድ ግምገማ ተካሄደ፤
በከተማ ደረጃ በተቋቋመ ግብረሃይል የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር ባለፉት ሦስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትና የቀጣይ ስምንት ወራት ዕቅድ ግምገማ ተካሄደ፤
================================
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ህዳር 7/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር ባለፉት ሦስት ወራት በተከናወኑ ተግባራትና በቀጣይ ስምንት ወራት ዕቅድ ግምገማ ተካሂዷል።
የግብረሃይሉን የሦስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት በንግድ ቢሮ የግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ጸጋዬ ደበሌ ሲሆን በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የተስተዋሉ ጥንካሬዎችና መታረም ያለባቸው ድክመቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
ግብረ ሃይሉ በቀጣይ 8 ወራት የሚያከናውናቸው የኑሮ ውድነት ቅነሳ ዝርዝር ተግባራት እቅድ በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የቀረበ ሲሆን፤ የምርት አቅርቦትን መጨመር ፣ የቅዳሜና እሁድ ገበያ መደረሻ ቦታዎች ቊጥርን ከ219 ወደ 240 ማሳደግና ምርቶችን መጨመር፣ ሽማች ማህበራትን ማሳደግ፣ የዳቦ ፋብሪካዎች መደገፍና ቁጥር መጨመር፣ የተኪና ኤክስፖርት ምርቶችን ጥራት ማሳደግ ትኩረት የሚደረግባቸው መሆናቸው ተግባራት መሆናቸውን ገልጸዋል።
የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ማምረት፤ መግዛትና መቆጣጠር ዋነኛ የመፍትሄ እርምጃዎች መሆናቸውን ያነሱት የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ለእቅዱ ስኬት የግብረ ሃይሉ አባላትና ተቋማት ተናበዉና ተቀናጅተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል።
እቅዱን ለመተግበር በሚከናወኑ ተግባራት ዙርያ ከተሳታ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments