መደበኛ ያልሆነ የንግድ ሥርዓት ማስያዝን በተመለከተ በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 184/17 ዓ.ም መሰረት የየቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ወደ ትግበራ መገባቱ ተገለጸ
መደበኛ ያልሆነ የንግድ ሥርዓት ማስያዝን በተመለከተ በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 184/17 ዓ.ም መሰረት የየቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ወደ ትግበራ መገባቱ ተገለጸ
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ንግድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መምጣቱ ይታወቃል
ይህም በመደበኛው የንግድ ሥርዓት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን በመገንዘብ ይህንን ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ በሥርዓት ካልተመራ በከተማ ውበት፣ገፅታ፤በከተማፅዳት፤በትራፊክ ፍሰትና እንቅስቃሴ፤በኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት እና በከተማ ሰላምና ፀጥታ አጠባበቅ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር የሚያስከትል ስለመሆኑ ይታመናል
በመሆኑ መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ የሚያስገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማግኘትና የሚያስከትላቸውን ችግሮች መቅረፍ የሚቻለው ዘርፉ ህጋዊ ሆኖ በስርዓት ሲመራ በመሆኑና ዘርፉን ሥርዓት በማስያዝ በዘርፉ የተሰማሩ ሰዎች ወደ መደበኛ የንግድ ሥርዓት እንዲገቡ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ቀደም ሲል በስራ ላይ የነበረው መደበኛ ያልሆነ ንግድ ሥራ ለመምራትና ሥርዓት ለማስያዝ የወጣ ደንብ ቁጥር 88/2009 አሁን ላለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዲጣጣም በማድረግ መተካት በማስፈለጉ የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካል ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ መሠረት ይህንን ደንብ 184/2017 አውጥቷል
በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት አዲስ ወደ ስራ የሚሰማሩ ነጋዴዎችን የተለዩ በ184/2017 ደንብ መሰረት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ወደ ትግበራ ከዚህ የሚከተለውን ስራ አከናውኗል፡፡
በ11ዱም ክፍለ ከተማ በጠቅላላ 227 አዲስ የስራ ቦታዎች የተለዩ ሲሆን 11112 መደበኛ ያልሆኑ ነጋዴዎችን ብዛት ተለይቶ ከተለዩት ውስጥ 4880 መደበኛ ያልሆኑ ነጋዴዎች በስታንዳርዱ መሰረት ወደ ስራ መግባታቸውን በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድ ግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ #ፀጋዬ ደበሌ ገልፀዋል፡፡
ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments