20ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ የንግድ ባዛርና ኤግዚብሺን ትርኢት መካሄድ ጀመረ።
20ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ የንግድ ባዛርና ኤግዚብሺን ትርኢት መካሄድ ጀመረ።
ህዳር 14/2018 ዓ.ም
"ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የፊታችን ህዳር 29 የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ ከተማ አቀፍ የንግድ ባዛር እና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በይፋ ተጀምሯል።
ኤግዚቢሽኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልካድር መርቀው በይፋ አስጀምረውቷል።
በኤግዚቢሽኑ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር ቀኑ ብሔር ብሔረሰቦች በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ተሰባስበው ደምቀው የሚታዩበት መሆኑን ገልፀው በተለይ ባለፉት ሰባት የለውጥ አመታት ቀኑን ከማክበር ባሻገር ብሔር ብሔረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደር መብታቸውን በተግባር ያረጋገጡበት መሆኑን አውስተዋል።
እንደ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር ገለፃ በባዛሩ ባዛሩ ሸማቾችን ከአገር በቀል አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማገናኘት የኢትዮጵያን እንግዛ ንቅናቄ እንዲዳብር በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
በኤግዚብሽኑ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ፀጋዬ ደበሌ በባዛሩ 130 የሚሆኑ አምራቾች ምርታቸውን የሚያቀርቡ መሆኑን ገልፀው የባዛሩ ዋና ዓላማ ሸማቹንና አምራቹን በማገናኘት የዋጋ ንረትን ይከላከላል ብለዋል።
ከንግድ ባዛሩ መክፈቻ ጎን የደም ልገሳ መርሃ-ግብር የተካሄደ ሲሆን ባዛሩ ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments