ቢሮው 20ኛው አለም አቀፍ የህፃናት ቀንን በማስመልከት ለሰራተኞች ስልጠና ሰጠ፤
ቢሮው 20ኛው አለም አቀፍ የህፃናት ቀንን በማስመልከት ለሰራተኞች ስልጠና ሰጠ፤
============+++==========
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ ህዳር 15/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ "የህፃናት ጥበቃና የመጫወት መብት ለሁሉም በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 20ኛው ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን በማስመልከት ለሁሉም ሰራተኞች ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናውን ያስጀመሩት በአዲስ የቢሮ የሰው ሀብት ልማትና ሥራ አመራር ዳይሬክተር አቶ ዳኒኤል ሚኤሳ ሲሆኑ መንግስት በአገራችን ብሎም በከተማችን በሁሉም የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ማህበራዊ አካታችነት እንዲኖር የሴቶች፣ የአረጋውያን፣ የህጻናት እና አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ፣ ለሁሉም በአመለካከቶቻቸው፣ ፍላጎቶቻቸው እና ተግባራቸው ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የህብረተሰባችን ክፍሎች በሁሉም ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞች እና ፕሮጀክቶች እቅድ አተገባበር ውስጥ በተጠና መልኩ በማካተት በመተግበር ላይ ይገኛል ብለዋል።
ለቢሮው ሰራተኞች ስልጠናውን የሰጡት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ አሉላ ሲሳይ ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት ሕፃናት ደሰተኛና ጤናማ ሆነው እንዲያድጉ የእያንዳንዱ ማህበረሰብ አባል ሚና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ አሉላ የሕፃናትን ደኀንነት፣ ኑሮ ፣ ጤና እና ትምህርት ለማሻሻል ግንዛቤና ትኩረት ማድረግ ይገባል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069351701097
https://t.me/Addisababatradebureau
https://vm.tiktok.com/ZMB4AxNvr/
https://youtube.com/@addisababatradebureau-s2d...
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments