"ላፍቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ገጠሩንና ከተማው...

image description
- In ንግደረ    0

"ላፍቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ገጠሩንና ከተማውን በማስተሳሰርና ገበያውን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው"

"ላፍቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ገጠሩንና ከተማውን በማስተሳሰርና ገበያውን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው"

የላፍቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ገጠሩንና ከተማውን በማስተሳሰርና ገበያውን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለፀ።

በዛሬው ዕለት በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ቃል በሁለተኛ ዙር በአዲስ አበባ ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች የላፍቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

ላፍቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከል በመዲናዋ አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ንረትን በመቀነስ ረገድ የጎላ አስተዋፅኦ እያደረጉ ከሚገኙ ገበያ ማዕከላት መካከል አንዱ መሆኑ በጉብኝት ወቅት ተመላክቷል።

ለጎብኚ አመራሮች ገለፃ ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ የላፍቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ገጠሩንና ከተማውን በማስተሳሰርና ገበያውን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አንስተዋል።

በገበያ ማዕከሉ አምራች አርሶ አደሮች ያሉ መሆኑን የገለፁት ኃላፊዋ ከነፃ ገበያው አኳያ ከ15 እስከ 20% የዋጋ ቅናሽ በማድረግ ምርቶችን ለተጠቃሚው እንደሚሸጡ ተናግረዋል።

በከተማው እየተከናወኑ በሚገኙ የሌማት ትሩፋት ስራዎች ከተማ አስተዳደሩ ሸማች ብቻ ሳይሆን አምራች መሆኑን የሚያሳዩ ምርቶች በገበያ ማዕከሉ የሚገኙ መሆኑንም አክለዋል::


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments