ባለፉት አምስት ወራት የኑሮ ውድነት እና በግብይ...

image description
- In ንግደረ    0

ባለፉት አምስት ወራት የኑሮ ውድነት እና በግብይት ውስጥ የሚስተዋሉ ፍትሀዊ ያልሆኑ የንግድ ውድድር ችግሮችን በመፍታት ረገድ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ።

ባለፉት አምስት ወራት የኑሮ ውድነት እና በግብይት ውስጥ የሚስተዋሉ ፍትሀዊ ያልሆኑ የንግድ ውድድር ችግሮችን በመፍታት ረገድ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ።

ህዳር 25/2018 ዓ.ም

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር ሚንስትር ክቡር አቶ ካሳሁን ጎንፌ በተገኙበት ሀገራዊ የንግድ ዘርፍ የሴክተር ጉባኤ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል።

በአገራዊ የንግድ ዘርፍ የሴክተር ጉባኤ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የቢሮውን የአምስት ወር የሥራ አፈፃፀም አቅርበዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ባቀረቡት ሪፖርት ባለፉት አምስት ወራት የኑሮ ውድነትን እና በግብይት ውስጥ የሚስተዋለውን ፍትሀዊ ያልሆነ የንግድ ውድድር ችግሮችን መፍታት የሚያስችል የአሠራር ስርዓት በመዘርጋት ውጤታማ ስራ መከናወኑን ገልፀዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ፣ ቢሮው በአምስት ወራት ውሰጥ 350 ሺ ዘመናዊ፣ ተደራሽና ቀልጣፋ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት አቅዶ 320 ሺ 865 ለሚሆኑት አገልግሎቱን መሰጠት መቻሉን ገልፀዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ በሪፓርታቸው ቢሮው ባለፉት አምስት ወራት 184 ሺ 010 በሚሆኑ የንግድ ድርጅቶች የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ አቅዶ 194 ሺ 450 ማከናወን የተቻለ መሆኑን ገልፀው በክትትል ወቅት ህገ-ወጥ የንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተው የተገኙ 10 ሺ 170 ድርጅቶች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል። ከእነዚህ ውስጥ 5 ሺ 595 የሚሆኑትን የንግድ ድርጅቶች ወደ ህጋዊነት መመለስ መቻሉን አብራርተዋል።

በቀረበው ሪፖርት መሠረት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ስድስት ዋና ዋና እንዲሁም 20 ንዑስ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ተገልጋዩ ባለበት (በኦንላይን) ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡ ከሌብነትና ብልሹ አሠራር ነፃ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ መቻሉ ተመላክቷል።

ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments