በከተማችን አዲስ አበባ አገልግሎት በሠስጠት ላይ...

image description
- In ንግደረ    0

በከተማችን አዲስ አበባ አገልግሎት በሠስጠት ላይ የሚገኙ ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት የዋጋ ግሽበትን በመከላከል ረገድ ድርሻቸው ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

በከተማችን አዲስ አበባ አገልግሎት በሠስጠት ላይ የሚገኙ ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት የዋጋ ግሽበትን በመከላከል ረገድ ድርሻቸው ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

ህዳር 17/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች የላፍቶ ዘመናዊ የንግድ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

"በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ቃል በሦስተኛ ዙር በአዲስ አበባ ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ የላፍቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከልን በአራት ዙር ጎብኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የገበያ ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ደበሌ እና ሌሎች የከተማችን ከፍተኛ አመራሮች ለሰልጣኞቹ የንግድ ማዕከሉን ተዟዙረው አስጎብኝተዋል።

አቶ ፀጋዬ ደበሌ ሰልጣኞቹን ባስጎበኙበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የላፍቶ ሁለገብ ገበያ 1.2 ቢልዮን ብር ወጪ ወጥቶበት በዘጠኝ ሄክታር ላይ ያረፈ ትልቅ ማዕከል መሆኑንን ገልፀው አምራች ኢንዱስትሪዎችና አርሶአደሮች ምርታቸውን አስከ 20 በመቶ በሚደርስ ቅናሽ በማቅረብ ለህብረተሰቡ እየሸጡበት እንደሚገኝ አብራርተዋል።

አቶ ፀጋዬ በገለፃቸው የላፎቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከል በከተማችን ለሚገኙ እሁድ ገበያዎች የአቅርቦት ምንጭ በመሆን በከተማች አዲስ አበባ የዋጋ ግሽበት እንዳይፈጠር በማድረግ ረገድ ድርሻው የጎላ መሆኑን አንስተዋል።

አቶ ፀጋዬ ደበሌ አክለውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመደመር ዕሳቤ መሠረት ገጠሩን ከከተማችን በንግድ ስርዓት ማስተሳሰር የቻሉ እና የዋጋ ንረትን በመከላከል ረገድ ጉልህ ሚና ያላቸው አምስት ዘመናዊ የንግድ ማዕከላት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments