የከተማ አስተዳደሩ በሚቢልዮኖች የሚቆጠር ማዋዕለ...

image description
- In ንግደረ    0

የከተማ አስተዳደሩ በሚቢልዮኖች የሚቆጠር ማዋዕለ ንዋይ በማውጣት ዘመናዊና ሁለገብ የገበያ ማዕከላትን ገንብቶ ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረጉ በከተማችን ሊከሰት ይችል የነበረን ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ጫና መከላከል መቻሉ ተገለፀ።

የከተማ አስተዳደሩ በሚቢልዮኖች የሚቆጠር ማዋዕለ ንዋይ በማውጣት ዘመናዊና ሁለገብ የገበያ ማዕከላትን ገንብቶ ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረጉ በከተማችን ሊከሰት ይችል የነበረን ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ጫና መከላከል መቻሉ ተገለፀ።

ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮልፌ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ሲካሄድ የቆየው የመሠረተ ልማት ግንባታ መጠናቀቁን ተከትሎ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በተገኙበት በማዕከሉ የንግድ ባዛር በይፋ ተጀምሯል።

ባባዛሩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የከተማ አስተዳደሩ የኮልፌ ሁለገብ የገበያ ማዕከልን በሙሉ አቅም ስራ ለማስጀመር ከፍተኛ በጀት መድቦ የመሠረተ ልማት ማሟያ ግንባታዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀው የዛሬው የባዛር ዝግጅት ማዕከሉ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለህብረተሰቡ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት መስጠት እየጀመረ መሆኑን ለማብሰር ጭምር ነው ብለዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ የከተማ አስተዳደሩ በሚቢልዮኖች የሚቆጠር ማዋዕለ ንዋይ በማውጣት ዘመናዊና ሁለገብ የገበያ ማዕከላትን ገንብቶ ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረጉ በከተማችን ሊከሰት ይችል የነበረን ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ጫና መከላከል መቻሉን አብራርተዋል።

በመድረኩ የኮልፌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወልዴ የተገኙ ሲሆን ማዕከሉ በሙሉ አቅሙ ስራ መጀመሩ የክ/ከተማው ነዋሪ የተለያዩ ምርቶችን በቅናሽ ዋጋ በአቅራቢያው እንዲያገኝ በማድረግ የዋጋ ግሽበትን በመከላከል ረገድ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments