የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ጋር በመሆን የአምስት ወራት የአፈፃፀም ውይይት መድረክ አካሄደ።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ጋር በመሆን የአምስት ወራት የአፈፃፀም ውይይት መድረክ አካሄደ።
ታህሳስ 06/2017 ዓ ም
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የአምስት ወራት አፈፃፀሙን ከንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ጋር በመሆን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
የቢሮው የአምስት ወራት አፈፃፀም በቢሮው የአገልግሎት አሠጣጥ ክትትል፣ ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ አብዮት ሀይሉ ከመድረክ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
ከመድረኩ ባለፉት አምስት ወራት ከገበያ አቅርቦት አንፃር የእሁድ ገበያዎችን እና የገበያ ማዕከላትን በማቀናጀት ከመሠረታዊ የፍጆታ ምርት አንፃር ለነዋሪው በቂ ምርት ማቅረብ በመቻሉ የዋጋ ግሽበትን በመከላከል ገበያውን ማረጋጋት እንደተቻለ ተገልጿል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ቢሮው ከዋና ዋና ግቦች አንፃር ውጤታማ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ገልፀው በቀጣዮቹ ወራት እቅዳችንን ሙሉ በሙሉ ለማሳካት በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ አክለውም በዕቅድ የተያዙ ተግባራትን ለማሳካት፣ አመራሩ ለፈፃሚው ተገቢውን ስምሪት ከመስጠት ባሻገር በቅርብ ሆኖ በመደገፍና በመከታተል ጠንካራ ጎኖችን የማስቀጠል እና በድክመት የታዩትን ደግሞ የማረም ሀላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments