የአዲስ አበባ ከተማን የአምስት ወራት የሸቀጦች...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አበባ ከተማን የአምስት ወራት የሸቀጦች አቅርቦትና ግብይትን የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት መነሻ ግኝቶች ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማን የአምስት ወራት የሸቀጦች አቅርቦትና ግብይትን የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት መነሻ ግኝቶች ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

ታህሳስ 06/2018 ዓ ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ የተጠሪ ተቋማትና የባለድርሻ አካላት አመራሮች በተገኙበት የከተማ አስተዳደሩን የባለፉት አምስት ወራት የሸቀጦች አቅርቦትና ግብይትን በተመለከተ ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት መነሻ ግኝቶች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

የዳሰሳ ጥናቱ ግኝቶች በቢሮው የገበያ መረጃ ጥናትና ፕሮሞሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ሙሰማ ከቀረበ በኋላ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።

የዳሰሳ ጥናቱን ማካሄድ ያስፈለገው የከተማችን ነዋሪ ቀጣይ የምግብ ነክ የፍጆታ ምርቶች ፍላጎትን በመለየትና በማወቅ አቅርበትን ማሟላት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ለማመላከት እንደሆነ ከመድረኩ ተገልጿል።

በውይይቱ የተሳተፉ አመራሮች በተካሄደው መነሻ የዳሰሳ ጥናት ዙሪያ ሊካተቱ ይገባል ያሉትን ነጥቦች ለጥናት ቡድኑ አቅርበዋል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ሀሳባቸውን ያጋሩት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ከመድረክ የተነሱ ሀሳቦችን እንደ ግብዓት በመውሰድ የዳሰሳ ጥናቱ እንዲከለስ እና የማጠቃለያ ግኝቶች በአጭር ጊዜ እንዲቀርቡ ለጥናት ቡድኑ አቅጣጫ ሰጥተዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments