በከተማ ደረጃ የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር ባለፉት...

image description
- In 2ኛው ከተማ ዓቀፍ "የኢትዮጵያን ይግዙ"    0

በከተማ ደረጃ የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር ባለፉት አምስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርትና በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገባቸው ተግባራትን የሚያሳይ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ በተቋቋመ ግብረ-ሃይል ግምገማ ተካሄደ፤

በከተማ ደረጃ የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር ባለፉት አምስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርትና በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገባቸው ተግባራትን የሚያሳይ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ በተቋቋመ ግብረ-ሃይል ግምገማ ተካሄደ፤

~~~~

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ 9/4/ 2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር ባለፉት አምስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርትና በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገባቸው ተግባራትን የሚያሳይ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ በተቋቋመ ግብረ-ሃይል ግምገማ ተካሄዷል።

ግምገማውን የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅና የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ልድያ ግርማ በጋራ መርተውታል።

በከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠርና ለመከታተል ከምርት አቅርቦትና ከንግድ ቁጥጥር አንጻር ባለፉት አምስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀረቧል።

ከቤቱ ለተነሱ ሃሳቦችና ጥያቄዎች የከተማችን ም/ከንቲባና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊው ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የንግድ ቢሮ ኃላፊዋ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅና የሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ልድያ ግርማ ማብራርያና ምላሽ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በቀጣይ ወራት የዋጋ ግሽበትን በከተማችን ወደ ነጠላ አሃዝ በማውረድ የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር ሊከናወኑ የሚገባቸው ተግባራት ላይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ግምገማዋ ተጠናቋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments