በከተማችን አዲስ አበባ የምግብ ዘይት አቅርቦትን...

image description
- In ንግደረ    0

በከተማችን አዲስ አበባ የምግብ ዘይት አቅርቦትን በማሳደግ የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር ሸማች ዩኒየኖች ከአምራቾች ጋር በትብብር ሊሠሩ ይገባል" ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ

"በከተማችን አዲስ አበባ የምግብ ዘይት አቅርቦትን በማሳደግ የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር ሸማች ዩኒየኖች ከአምራቾች ጋር በትብብር ሊሠሩ ይገባል" ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ

ታህሳስ 13/2018 ዓ ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አመራሮች በከተማችን አዲስ አበባ ከሚገኙ የሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩነየን እና ከአዲስ አበባ ንግድ ስራዎች ድርጅት ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቡልቡላ አግሮ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በመገኘት የዘይት ማምረቻ ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በከተማችን አዲስ አበባ የዘይት አቅርቦትን በማሳደግ ዋጋውን መቆጣጠርና የተረጋጋ ገበያ ለመፍጠር ነው ተብሏል።

በጉብኝቱ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ባደረጉት ንግግር በከተማችን አዲስ አበባ የምግብ ዘይት አቅርቦትን በማሳደግ የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር ሸማች ዩኒየኖች ከአምራቾች ጋር በትብብር መስራታቸው ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ አያይዘው የህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየኖች በቀጥታ ከአመራቾች ጋር በመነጋገር እና በመቀራረብ መስራታቸው በመሀል ሊኖር የሚችለውን አላስፈላጊ የገበያ ሰንሰለት በማስቀረት የዋጋ ንረትን መከላከል ያስችላል ብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments