የሸማቾችን መብት ማስጠበቅ የተረጋጋ የገበያ ሥር...

image description
- In ንግደረ    0

የሸማቾችን መብት ማስጠበቅ የተረጋጋ የገበያ ሥርዓት ለመፍጠር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ።

የሸማቾችን መብት ማስጠበቅ የተረጋጋ የገበያ ሥርዓት ለመፍጠር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ።

ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ወረዳ ድረስ ለሚገኙ የሸማች መብት ጥበቃ ቡድን መሪዎች በሽማቾች መብት ጥበቃ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር የሸማቾች መብት ጥበቃ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰይፉ አየለ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን አላማውም በሽማቾች መብት ጥበቃ ምንነት፣ አስፈላጊነት እና አተገባበር ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲያዝ በማድረግ ሥራው በእውቀት እንዲመራ ማስቻል ነው ብለዋል።

በስልጠና መደረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ስመኘው ተሾመ የሸማቾችን መብት ማስጠበቅ የተረጋጋ የገበያ ሥርዓት ለመፍጠር ወሳኝ ሚና የሚጫወት መሆኑን ገልፀው ለዚህ ደግሞ ታችኛው መዋቅር ድረስ የሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

አቶ ስመኘው አክለውም የከተማ አስተዳደሩ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ መድቦ ዘመናዊ የገበያ ማዕከላትን በመገንባትና የንግድ ስራዎች ድርጅትን በማቋቋም ህብረተሰቡን ከአላስፈላጊ የኑሮ ውድነት በመከላከል የተረጋጋ የገበያ ሥርዓት መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments