የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጪውን የገና በዓል ም...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ የንግድ ባዛሮችን በይፋ አስጀመረ።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ የንግድ ባዛሮችን በይፋ አስጀመረ።

ታህሳስ 24/2018 ዓ ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በ11 ክ/ከተሞች ከዛሬ ታህሳስ 24/2018 ዓ ም ጀምሮ የንግድ ባዛሮችን በይፋ ሥራ እንዲጀምሩ አድርጓል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በየካ ክ/ከተማ ተገኝተው የንግድ ባዛሩን መርቀው ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የከተማ አስተዳደሩ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀው በቂ የሆነ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ይገኛል ብለዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ አክለውም የከተማ አስተዳደሩ ለበዓል ካስጀመራቸው ባዛሮች በተጨማሪ ከአርሶ አደሮችና ከአምራቾች ጋር ቀጥታ በመገናኘት በአምስት የገበያ ማዕከላት፣ በ239 እሁድ ገበያዎች፣ በአዲስ አበባ ንግድ ሥራዎች ድርጅትና በህብረት ሥራ ሸማች ማህበራት ዮኒየኖች በቂ ምርቶች ገብተው በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ይገኛል ብለዋል።

በመጨረሻም ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መጪው የገና በዓል የደስታ እና የጤና እንዲሆን ተመኝተዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments