የምርታማነት እምርታ ለዘላቂ ከፍታ በሚል መሪ ቃል መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቶች የሚቀርቡበት ደማቅ የበዓል ባዛር ተከፈተ።
የምርታማነት እምርታ ለዘላቂ ከፍታ በሚል መሪ ቃል መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቶች የሚቀርቡበት ደማቅ የበዓል ባዛር ተከፈተ።
ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ መጪውን የገና በዓል አስመልክቶ የአቅርቦት ችግር እንዳያጋጥም እና የምርታማነት እምርታ ለዘላቂ ከፍታ በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት የተከፈተው ባዛር ጥራቱን የጠበቀ በቂ የምርት አቅርቦት አምራቹን ቀጥታ ከሸማቹ ማህበረሰብ በማገናኘት አንፃራዊ የሆኑ የግብይ ስርዐት ለማሳካት በዓላትን በቅንጅት በመስራት የፍጆታ እቃዎች በተከታታይ በማቅረብ ዘላቂ የግብይት ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በባዛሩ በርካታ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በስፋትና በጥራት የቀረቡበት መሆኑንና ባዛሩ የበዓል ገበያን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለዉ በመግለፅ የክ/ከተማው ማህበረሰብ በባዛሮቹ በመገኘት የተለያዩ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገበይጥሪ አቅርበዋል።
በባዛሮቹ የህብረት ስራ ሸማች ማህበራት የተለያዩ ምርቶችን እያቀረቡ እንደሚገኝ ተገልጿል።
#Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments