መጪው የገና በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀው የጊዮርጊስ አደባባይ ባዛር በይፋ ተከፈተ።
መጪው የገና በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀው የጊዮርጊስ አደባባይ ባዛር በይፋ ተከፈተ።
ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም
መጪው የገና በዓል ገበያን ለማረጋጋት የተዘጋጀው የጊዮርጊስ አደባባይ ባዛር የከተማና የክ/ከተማ አመራሮች በተገኙበት በይፋ ለግብይት ክፍት መደረጉን የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታወቋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱር ቃድር ሬድዋን መጪው የገና በአልን አስመልክቶ አምራች ሻጭና ሸማች የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመጥቀም የተዘጋጀ ባዛር መሆኑን ተናግረዋል።
ሸማቹ በአዲስ የበዓል ገበያ አማራጭ በአቅራቢያው በተመጣጠነ ዋጋ የሚገበይበት ባዛር መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም በተረጋጋ ሁኔታ ግብይት በመፈፀም በዓሉን ማክበር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
የተከፈተው ባዛር እና ከእሁድ ገበያዎችና የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች በተደማሪነት የኑሮ ጫና የሚቀንሱ መሆናቸውን ተመላክቷል።
ባዛሩ ደረጃውን (ስታንዳርድ) የጠበቀና አስፈላጊ የበዓል ምርት ግብዓቶች ተሟልተው በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ በማድረግ ገበያ እንዲረጋጋ አስተዳደሩ ዝግጅት ሲያደረግ መቆየቱ በመክፈቻው ሰዓት ተገልጿል።
የአራዳ ክ/ከተማ የጊዮርጊስ አደባባይ ባዛር ከዛሬ ጀምሮ እስከ በዓሉ ዋዜማ በተሟላ የምርት አቅርቦት እንደሚቀጥል አስተዳደሩ አመላክቷል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments