ለበዓል የሚሆኑ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተ...

image description
- In ንግደረ    0

ለበዓል የሚሆኑ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየቀረበ መሆኑ ተገለፀ።

ለበዓል የሚሆኑ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየቀረበ መሆኑ ተገለፀ።

ታህሳስ 25/2017 ዓ ም

የኢፌዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር ሚንስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎንፌ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማን የግብይት ሁኔታ ተዟዙረው ጎብኝተዋል።

ዶ/ር ካሳሁን ጎንፌ በክ/ከተማ ደረጃ የተከፈቱ የበዓል ባዛሮችን እና የሸጎሌ የቁም እንስሳ የገበያ ማዕከልን ተዟዙረው ከጎበኙ በኋላ በሰጡት አስተያየት ለበዓል የሚሆኑ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየቀረ መሆኑን መመልከታቸውን ገልፀዋል።

ዶ/ር ካሳሁን አያይዘው እንደ አገር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ በመቻሉ ዋና ዋና የፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ እየቀረበ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ክቡር ሚንስተሩን ካስጎበኙ በኋላ በሰጡት አስተያየት የከተማ አስተዳደሩ ቀድሞ በሠራቸው ስራዎች የበዓል ፍጆታ በበቂ ሁኔታ ወደ ከተማው እንዲገባ መደረጉን ገልፀው ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች በተለይም የቁም እንስሳ፣ የሽንኩርት፣ የጤፍ እና የቲማቲም ዋጋ በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ እየቀረቡ መሆናቸውን አብራርተዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments