በከተማችን አዲስ አበባ የንግድ ሥርዓቱን ፍትሀዊ...

image description
- In ንግደረ    0

በከተማችን አዲስ አበባ የንግድ ሥርዓቱን ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች ስኬታማ መሆናቸው ተገለፀ።

በከተማችን አዲስ አበባ የንግድ ሥርዓቱን ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች ስኬታማ መሆናቸው ተገለፀ።

ጥር 01/2018 ዓ ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የገበያ ማረጋጋት፣ የህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥርና የአዲስ አበባ ታምርት ግብረ-ሀይልን የሁለት ወራት አፈፃፀም በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

የግብረ ሀይሉ የህዳር እና የታህሳስ ወር አፈፃፀም ሪፖርት ከመድረክ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።

በውይይት የቢሮው ጠቅላላ አመራር እና የክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በአፈፃፀም ሂደት የታዩ ጠንካራ ጎኖች እና ክፍተቶች ተነሰተው ቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ግብረ-ሀይሉ ያከናወናቸው ተግባራት የንግድ ሥርዓቱን ፍትሀዊነት ከማረጋገጥ አንፃር ውጤታማ መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይ ይህንኑ አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments