በከተማችን አዲስ አበባ የንግድ ሥርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ባለፉት ሁለት ወራት የተሠሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸው ተገለፀ።
በከተማችን አዲስ አበባ የንግድ ሥርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ባለፉት ሁለት ወራት የተሠሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸው ተገለፀ።
ጥር 03/2017 ዓ ም
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ የገበያ ማረጋጋት፣ የህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥርና የአዲስ አበባ ታምርት ግብረ-ሀይልን የሁለት ወራት አፈፃፀም በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ከወረዳ ጀምሮ የሚገኙ የግብረ-ሀይሉ አባላት በተገኙበት የሁለት ወር አፈፃፀም ሪፖርት በቢሮው የግብይት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ በአቶ ፀጋዬ ደበሌ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።
ክቡር አቶ ጃንጥራር ከውይይቱ በኋላ በሰጡት ሀሳብ እንደ ከተማ አስተዳደር የንግድ ሥርዓቱን ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ ባለፉት ሁለት ወራት የተሠሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ገልፀዋል።
አቶ ጃንጥራር አክለውም በክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ የተቀመጡ ኢኒሼቲቮችን ከማሳካት አንፃር አሁንም የዋጋ ንረትን ይበልጥ ለመቀነስና ምርታማነትን ለማስቀጠል መስራት ይገባል ብለዋል።
እንደ ክቡር አቶ ጃንጥራር ገለፃ ባለፉት ሁለት ወራት የተመዘገቡ ውጤታማ አፈፃሞችን ሳይቆራረጡ አመቱን ሙሉ ለማስቀጠል ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በመድረኩ በሰጡት አስተያየት በክልሎች ምርትና ምርታማነት ማደግ በመቻሉና ይህንኑ በመጠቀም ምርቶች ከአርሶ አደሩ በቀጥታ ወደ ከተማችን ማስገባት በመቻላችን የዋጋ ግሽበትን መቀነስ ተችሏል ብለዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ እንደ ከተማ አስተዳደር የግብርና ምርትቶችን በተለይም የዶሮ፣ የእንቁላል፣ የወተት እና የዘይት መርቶችን ለማሳደግ በቅንጅትና በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments