ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል የክትትልና የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ።
ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል የክትትልና የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ።
አዲስ አበባ የካቲት 10/2018 ዓ.ም.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ የቀጣይ 6 ወራት ዕቅድ ክለሳ አፈጻጸሙን ከክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎች ጋር ገምግሟል፡፡
የቢሮው የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ አሰፋ የዕቅድ ክለሳ አፈፃፀሙን አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል።
የንግድ ቢሮ ገበያ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፈ አቶ ፀጋዬ ደበሌ በውይይቱ ባደረጉት ንግግር ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ከመቆጣጠር አንፃር በየደረጃው የሚገኙ የቢሮው መዋቅሮች በቅንጅት ሊሠሩ ይገባል ብለዋል።
እንደ አቶ ፀጋዬ ገለፃ በከተማችን አዲስ አበባ በነዳጅም ሆነ በሌሎች አቅርቦቶች ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ ህገ ወጥ ተግባራትን ለመከላከል የክትትልና የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments