ቢሮው ከምስራቅ ሸዋ ኦሮሚያ ክልል አርሶ አደሮች ጋር በምርት አቅርቦት ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሄደ።
ቢሮው ከምስራቅ ሸዋ ኦሮሚያ ክልል አርሶ አደሮች ጋር በምርት አቅርቦት ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሄደ።
የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ/ም
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከምስራቅ ሸዋ ኦሮሚያ ክልል አርሶ አደሮች ጋር በምርት አቅርቦት ዙሪያ በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
የቢሮው ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ገመቹ ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ከተውጣጡ አርሶ አደሮች ጋር በምርት አቅርቦት ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሂደዋል።
ከአርሶ አደሮቹ ጋር በተካሄደ ውይይት በከተማችን አዲስ አበባ አምስቱም መግቢያ በሮች የተገነቡ ግዙፍ የገበያ ማዕከላቶች ውስጥ በቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖር በቅንጅት ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያ ሀሳባቸውን ያካፈሉት የቢሮው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ በከተማችን አዲስ አበባ የምርት እጥረት እንዳይፈጠር ቢሮው ከአጎራባች ክልሎችና ከተሞች ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069351701097
https://t.me/Addisababatradebureau
https://vm.tiktok.com/ZMB4AxNvr/
https://youtube.com/@addisababatradebureau-s2d...
https://x.com/ambomoti32832?s=21
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments