በአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የ...

image description
- In ንግደረ    0

በአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የተመራ የልዑካን ቡድን የገበያ ትስስርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጋር ተወያይተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የተመራ የልዑካን ቡድን የገበያ ትስስርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጋር ተወያይተዋል።

የካቲት 16/2018 ዓ ም

በውይይቱ በዞኑ የግብርና ምርቶች በስፋት የሚመረቱ ቢሆንም፣ የግብይት ክፍተት እንዳይፈጠር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር የገበያ ትስስሩን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ተመላክቷል።

በውይይቱ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ "ምርቶችን ወደ ማዕከላዊ ገበያ ማውጣት የዞኑን የኢኮኖሚ አቅም ከማሳደጉም ባለፈ የአምራቹን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የተረጋጋ ግብይት ለመፍጠር ወሳኝ ነው ብለዋል።

​ከአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ የመጡ ልዑካን በበኩላቸው ትስስሩ በዋናነት ገበያን ለማረጋጋት፣ ትኩስ ምርቶችን ለተጠቃሚው ለማድረስና አምራቹን ከሸማቹ በቀጥታ ለማገናኘት ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።

​በመጨረሻም የጋሞ ዞን ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ የተጀመረውን የገበያ ትስስር በኃላፊነት ለማጠናከር እንደሚሰራ ተገልጿል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments