20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአለ አከባበር ላይ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማት፣ ክ/ከተሞች የእውቅና እና የምስጋና ሽልማት ተበረከተላቸው።
20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአለ አከባበር ላይ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማት፣ ክ/ከተሞች የእውቅና እና የምስጋና ሽልማት ተበረከተላቸው።
የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመሳተፍ ወደ መዲናችን የመጡ እንግዶችን በክብር በመቀበል፣ በማስተናገድ እና በክብር እስከ መሸኘት በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና የክ/ከተማ ም/ቤቶች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በበዓሉ ላይ የነበሩ ዋና ዋና ተግባራት ማለትም ከህገ መንግስት አስተህምሮ ጀምሮ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከመፍጠር ፤ ትስስርና አንድነትን ከማጠናከር እንዲሁም ከገበያ ትስስር እና ገጽታ ግንባታ አኳያ አመርቂ ስራ መሰራቱንም የተከበሩ አፈ ጉባኤ ጨምረው ገልፀዋል።
በመድረኩ ላይ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ተቋማት እና ክፍለከተሞች የምስጋና የምስክር ወረቀት ከተከበሩ አፈ ጉባኤ እጅ ተቀብለዋል::
On the 20th Ethiopian Nations, Nationalities and Peoples Day celebration, the institutions, sub-cities have given recognition and appreciation awards.
The Addis Ababa City Assembly Speaker Mrs. Buzena Alkedir who delivered a welcome message has expressed her gratitude to the institutions and sub-city councils who contributed to the successful completion of the 20th Ethiopian Nations, Nationalities and Peoples Day celebration.
The honorable speaker of the assembly stated that the main activities of the holiday are from teaching the constitution, creating people-to-people relations, strengthening ties and unity, and building the market links and building the appearance.
Institutions and sub-cities that have contributed greatly on the stage have received certificates of appreciation from the honorable speaker.
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments