የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሮመዳን ወር/ኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓል ባዛር በይፋ አሰጀመረ።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሮመዳን ወር/ኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓል ባዛር በይፋ አሰጀመረ።
የካቲት 04/2018 ዓ ም
የበዓል ባዛሮቹ በ11ዱም ክ/ከተሞች የተዘጋጁ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እና ሌሎች የከተማችን ከፍተኛ አመራሮች ባዛሮቹን በይፋ አስጀምረውታል።
በልደታ ክ/ከተማ የተካሄደውን የኢድ አልፈጥር በዓል ባዛሩን መርቀው የከፈቱት ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ባደረጉት ንግግር የከተማ አስተዳደሩ በከተማችን አዲስ አበባ የዋጋ ንረትን ከመከላከል እና የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት ከማረጋገጥ አንፃር ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ የቻሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወን መቻሉን ገልፀዋል።
እንደ ወ/ሮ ሀቢባ ገለፃ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የዕሁድ ገበያዎችን የማስፋፋት ሁለገብ የገበያ ማዕከላትን በማስፋፋት የፍጆታ ምርቶችን እስከ 20 በመቶ ቅናሽ በማቅረብ ገበያውን በዘላቂነት ማረጋጋት ችሏል ብለዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አያይዘውም ቢሮው በየወቅቱ የሚያዘጋጃቸው የበዓል ባዛሮች በበዓል ወቅት ሊከሰት የሚችልን የዋጋ ንረት በመከላከል ገበያውን በማረጋጋት ረገድ የማይተካ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069351701097
https://t.me/Addisababatradebureau
https://vm.tiktok.com/ZMB4AxNvr/
https://youtube.com/@addisababatradebureau-s2d...
https://x.com/ambomoti32832?s=21
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments