በከተማችን አዲስ አበባ የነዳጅ ስርጭት ፍትሀዊነ...

image description
- In 2ኛው ከተማ ዓቀፍ "የኢትዮጵያን ይግዙ"    0

በከተማችን አዲስ አበባ የነዳጅ ስርጭት ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ።

በከተማችን አዲስ አበባ የነዳጅ ስርጭት ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ።

መጋቢት 05/2018 ዓ ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከፌደራል ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነዳጅ ማደያዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በውይይቱ ከወረዳ እስከ ማዕከል የሚገኙ የአዲስ አበባ የገበያ ማረጋጋት፣ ህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር እና የኢትዮጵያ-አዲስ አበባ ታምርት ግብረ-ኃይል አባላት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አመራሮችና እና የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ባለቤቶች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነዳጅ ማደያዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቃኘት የተካሄደ የመስክ ስራ ሪፖርትን ከመድረክ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር በከተማችን አዲስ አበባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከነዳጅ ስርጭት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮች በአስፈፃሚ አካላትና በነዳጅ ማደያዎች ተቀናጅተው የሚፈፅሙት መሆኑን ገልፀው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሠሩ ይገባል ብለዋል።

አቶ ጃንጥራር አባይ አያይዘውም መንግስት በችግሩ ላይ ተሳትፎ ያላቸውን አካላት በመለየት አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገልፀው ከፍተኛ ድጎማ ተደርጎበት ከውጪ የሚገባው ነዳጅን ነዳጅ አቅራቢዎች በፍትሃዊነት የማሰራጨት ሀላፊነት አለባቸው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በመድረኩ በሰጡት አስተያየት ከነዳጅ ስርጭት ጋር ተያይዞ በማደያዎች የሚፈፀሙ ችግሮች ሰፊ መሆናቸው ገልፀው ችግሩን ለመፍታት ቢሮው የቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የፌደራል ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ደስታ በውይይቱ በሰጡት ሀሳብ በየደረጃው በነዳጅ ማደያዎች ብዙ ተዋናዮች የሚሳተፉበት የሌብነት ችግር መኖሩን በማንሳት ኤጀንሲው ችግሩን ለመቆጣጠር ከፍትህ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments