የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓል ባዛር በይፋ አሰጀመረ።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓል ባዛር በይፋ አሰጀመረ።
መጋቢት/2018 ዓ ም
የበዓል ባዛሮቹ በ11ዱም ክ/ከተሞች የተዘጋጁ ሲሆን የኢፌድሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር ሚንስቴር ዶ/ር ካሳሁን ጎንፌ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ዣንጥራር አባይ፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እና ሌሎች የከተማችን ከፍተኛ አመራሮች ባዛሮቹን በይፋ አስጀምረውታል።
በቂርቆስ ክ/ከተማ የተካሄደውን የትንሳኤ በዓል ባዛር መርቀው የከፈቱት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር ሚንስቴር ዶ/ር ካሳሁን ጎንፌ ባደረጉት ንግግር መንግስት የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ከመገንባት ጀምሮ ምርታማነትን ለማሳደግ የሰራው ስራ ውጤት በማምጣቱ የዋጋ ንረትን መከላከል ተችሏል ብለዋል።
የፍጆታ አቅርቦት ችግር አለመኖሩን የገለፁት ዶክተር ካሳሁን ጎንፌ ወቅታዊውን የመካከለኛው ምስራቅ ችግር እንደ ሰበብ በመውሰድ በምርት ላይ አግባብነት የሌለው የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ፣ ምርት በሚያከማቹና በሚደብቁ ላይ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።
ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎንፌ አያይዘውም የዘንድሮውን በዓል ምክንያት በማድረግ በተከፈቱ ባዛሮች ላይ በቂ ምርት መቅረቡን ገልፀው የከተማው ነዋሪ በባዛሮቹ ተገኝቶ እንዲገበያይ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በባዘሩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የከተማ አስተዳደሩ በከተማችን አዲስ አበባ የዋጋ ንረትን ከመከላከል እና የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት ከማረጋገጥ አንፃር ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ የቻሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወን መቻሉን ገልፀዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አያይዘውም ቢሮው በየወቅቱ የሚያዘጋጃቸው የበዓል ባዛሮች በበዓል ወቅት ሊከሰት የሚችልን የዋጋ ንረት በመከላከል ገበያውን በማረጋጋት ረገድ የማይተካ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments