መጪውን የኢድ አልአድሃ አፈፋ በዓል ምክንያት በማድረግ በቂ የቁም እንስሳ እና የፍጆታ ምርት አቅርቦት መኖሩ ተገለፀ።
መጪውን የኢድ አልአድሃ አፈፋ በዓል ምክንያት በማድረግ በቂ የቁም እንስሳ እና የፍጆታ ምርት አቅርቦት መኖሩ ተገለፀ።
ግንቦት 17/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በከተማችን አዲስ አበባ ከሚገኙ የቁም እንስሳ አቅራቢዎች እና ከአምራቾች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ መጪውን የኢድ አል-አደሃ አረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ በከተማቸውን በቂ የቁም እንስሳ እንዲሁም ሌሎች የፍጆታ ምርቶች መግባታቸው ተገልጧል፡፡
ውይይቱን የመሩት የቢሮው የገበያ ማዕከላት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ሀሰኑ በዓልን ምክንያት በማድረግ አርቴፊሻል ዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ደላላውን በማስወጣት ምርቶች በቀጥታ ከአምራቹ ወደ ገበያ ማዕከላት እንዲገቡ ለማድረግ ትኩረት ተደርጎ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡
አቶ ሽመልስ አያይዘውም በበዓል ወቅቶች በፍጆታም ሆነ በቁም እንስሳ ምርቶች ላይ ያለአግባብ ዋጋ ሊጨምሩ የሚችሉ የደላላ ጣልቃ-ገብነትን፣ የምርት መሸሸግና ሌሎች ምክንያቶችን በመለየት በንግድ ህጉ መሰረት እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ገለፀው ለመጪው በዓልም በቂ ምርት በመኖሩ ህብረተሰቡ በገበያ ማዕከላት በመሄድ እንዲገበያይ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments